Hesperian Health Guides

አዲስ የተወለዱ ሕፃናት የጤና ችግር

ይህ ምእራፍ ውስጥ፦

ጤናማ ሕፃን ያለችግር መተንፈስ ይችላል። ሕፃኑ ጡት በየ2 እስከ 4 ሰዓት መጥባት አለበት እና ሲርበው ወይንም ጨርቁን ሲያረጥብ በራሱ መነሳት መቻል አለበት። የተወለደ ሕፃን ቆዳው ንጹ ወይንም ትንሽ ቅላት ወይንም ከትንሽ ቀን በኃላ የሚጠፋ መንደብደብ ሊኖረው ይችላል። እነዚህን ምልክቶች ካልታዩ ቶሎ ሕፃኑ እርዳታ ያስፈልገዋል።

አዋቂን ለመግደል ቀናት የሚወስድ በሽታ ሕፃንን በትንሽ ሰዓት ሊገል ይችላል

ኢንፌክሽን

ለተወለደ ሕፃን ኢንፌክሽን አደገኛ ስለሆነ ወድያውኑ በአንቲባዮቲክ(antibiotics) መታከም አለበት። አካባቢያችሁ የጤና ጣቢያ ካለ እዚያ ቶሎ መሄድ። ካለዚያ የጤና ጣቢያውን ርቀት እና ያላችሁን መድኃኒት በማመዛዘን ቶሎ ዕርዳታ ማግኘት ወይንም መድኃኒት እናንተው መስጠት ምንም እንኳን በመንገድ እርዳታ ለማግኘት እየሄዳችሁም ቢሆን።

አደገኛ ምልክቶች
 • ፈጣን አተነፋፈስ፦ ሲተኙ ወይንም ሲያርፉ በደቂቃ ከ60 በላይ ከተነፈሱ
 • አየር ለማግኘት መታገል፦ ሕፃን ሲተኛ ወይንም ሲያርፍ ደረት ወደውስጥ መሳብ፣ አየር ለመሳብ የጥረት ድምጽ ሲሰማ፣ የአየር መውሰድ ጥረት አፍንጫን ሲገፋ
NWTND Newb Page 12-1.png
ደረት ወደውስጥ መሳብ
አፍንጫ ትንፋሽ ሲገፋ
 • ትኩሳት ከ37.5º ሴንቲግሬድ በላይ ወይንም በጣም ሲቀዘቅዙ ከ35.5ºሴንቲግሬድ በታች
 • ሀይለኛ መንደብደብ ከብዙ ብጉር ጋር ወይንም የቆዳ መነፋፋት (ትንንሽ መንደብደብ የተለመደ ነው)
 • አለመመገብ
 • አልፎ አልፎ ብቻ ከእንቅልፍ መነሳት እና ምንም መልስ ከሕፃን አለማየት ለምታረጉት ነገሮች
 • መንቀጥቀጥ፦እራስ መሳት ወይንም የመፈራገጥ ንቅናቄ

ከላይ የተጠቀሱት ነገሮች የኢንፌክሽን ምልክት ሊሆኑ ስለሚችል ሕፃኑ ህክምና ያስፈልገዋል።


ህክምና

ኢንፌክሽን ከጠረጠራችሁ ግን ኀይለኛ ካልሆነ ወድያውኑ አምፒሲሊን(Ampicillin) ወይንም አሞክስሊን(Amoxicillin) ስጡ። ኢንፎክሽኑ ኀይለኛ ከሆነ ወድያውኑ አምፒሲሊን(Ampicillin) እና ጀንታሚሲን(gentamicin) መከተብ እና የህክምና እርዳታ ባስቸክዋይ መፈለግ። ምን ያህል መሰጠት እንዳለበት የሕጻኑ ኪሎ ይወስነዋል።

ሕጻኑ በሁለተኛው ቀን እየተሻለው መምጣት አለበት።በሁለተኛው ቀን እየተሻለው ካልመጣ ሌላ ዓይነት አንቲባዮቲክ(antibiotics) ያስፈልጋል።

የክኒን አንቲባዬቲክ ተፈጭቶ ከእናት ወተት ጋራ ተቀላቅሎ ሊሰጥ ቢቻልም አንዳንድ አንቲባዬቲክ በመርፎ ክትባት መሰጠት አለባቸው። በመርፌ/በክትባት የሚሰጠው አንቲባዬቲክ መድኃኒት የጎን ረጅም የታፋ ጡንቻ ላይ ይሁን።ለተጨማሪ ማብራርያ እንዴት ክትባት በትክክል እንደሚሰጥመድኃኒት፣ምርመራ፣እና፣ሕክምናን እዩ (በመቀናበር ላይ ነው)

NWTND Newb Page 13-1.png

በምጥ ግዜ እናት ትኩሳት ካላት ከላይ የተጠቀሱት አደገኛ ምልክቶች ሕፃን እንዳለው ወይንም እንደሌላው በደንብ መከታተል ያስፈልጋል።በተጨማሪ ሕፃኑ መኀጸን ውስጥ አይነ ምድር ካደረጉ አይነ ምድሩን ወደ ውስጥ ሊተነፍሱ ይችላሉ። (አይነ ምድር መኀጸን ውስጥ አርገው ከሆነ ውሀው ቡና አይነት ነገሮች ወይንም ቀለሙ አረንጎዴማ ይመስላል ወይንም የሕፃኑ ቆዳ ቢጫማ/ለየት ያለ ይሆናል።) ይህ የሳንባ ኢንፌክሽን በትንሽ ቀን ውስጥ ሊያመጣ ስለሚችል የኢንፌክሽን ምልንክቱ ሲታይ ሕፃኑን ቶሎ ለማሳከም/ለማከም ዝግጁ መሆን ያስፈልጋል።

ማልቀስ

አባት ልጅን ይዞ እናትን እያናገረ
አንቺ ስታርፊ እኔ ልጃችንን ልንከባከብ

አንዳንድ ሕፃናት በኀይል ከሌሎች ሕፃናት የበለጠ ያለቅሳሉ ግን የጤና ችግር ምልክቶች እስካልታየባቸው ድረስ ደህና ናቸው።ለማረጋገጥ በማታለቅስበት ጊዜ ሕፃንዋ ትክክል እንደምትተነፍስ አረጋግጡ።

ተከታታይ እና ረዘም ያለ ለቅሶ ምሽት ላይ የሚብስ ኮሊ ይባላል። በሶስት ወር ውስጥ እየተሻለ ይሄዳል ተብሎ ይገመታል። ይህ ከሕጻኑ ይልቅ ለቤተሰብ ችግር ነው። ይህንን በመረዳት ለእናት ደግ ሁኑ እና በቂ ዕረፍት እና እርዳታ እናት እንድታገኝ አርጉ።

ሕጻንዋ ቀኑን ሙሉ በአብዛኛውን ጊዜ ካለቀሰች፣አልመገብም ካለች እና ትኩሳት ወይንም የመተንፈስ ችግር ካላት የኢንፌክሽን ምልክት ሊሆን ይችላል

ማስታወክ

NWTND Newb Page 14-1.png

አንዳንዴ ወተት ከበዛ ሕፃናት ወተት በአፋቸው ወይንም በአፍንጫ ያቀረሻሉ። ሕፃን በተገቢ እስከጠባ እና ኪሎ እስከጨመረ ማቀርሸት ምንም አደገኛ አይደለም። ልጅ ከጠባ በኋላ ወደ ላይ ከፍ አርጋችሁ ያዙ። በቀላሉ ወተቱ ከልጅ ከፈሰሰ ማቀርሸት ሲሆን የልጅ ሰውነት ደግሞ ሀይል ሲያቀረሽ ከተጠቀመ ማስመለሰ ነው።

አደገኛ ምልክቶች
 • በተደጋጋሚ ማስመለስ ወይንም ሆድ ውስጥ ምግብ አለመቆየት
 • ደም ማስመለስ
 • በቂ ፈሳሽ ሰውነት ውስጥ አለመኖር (ዲሀይድሬሽን)
ሕፃንን ማስገሳት
ሕጻኑ ከጠባ በኋላ ትከሻ ላይ ወይንም ጉልበት ላይ አርጋችሁ በቀስታ ጀርባውን መታ መታ በማድረግ እንዲያገሳ አርጉ።

ውሀ ሰውነት ውስጥ ማነስ (ዲሀይድሬሽን)

የሕፃናት ሰውነት በቀላሉ ውሀ ስለሚያጣ የሰውነት ውሀ ማጠር ለሕፃናት አደገኛ መሆኑን ማወቅ ያስፈልጋል

ምክንያቱ
 • ተቅማጥ
 • ትውከት
 • ከሁለት እስከ አራት ሰዓት ጊዜ ውስጥ አለማጥባት
 • የእናት ጡት ያልሆነ ወተት መመገብ (እንደ ፎርሙላ፣ ወተት፣ ወይንም ውሀ)
 • ሙቅ የአየር ጠባይ
ምልክት
 • ትንሽ መሽናት፣ጠቆር ያለ ሽንት፣ ሀይለኛ ሽታ ያለው
 • ደረቅ አፍ እና ደረቅ ምላስ
 • የፈዘዘ ዓይን ወይንም ከተለመደው ውጭ የሆነ አይነት ቆዳ

ሀይለኛ ውሀ ማጠር የጐደጐዱ ዓይን፣ ለስላሳ እና የጐደጐዱ ቦታዎች ጭንቅላት ላይ መታየት፣ የኪሎ ማነስ፣ ወይንም ብዙ አለመነቃነቅ/ያለመንቃት ሊያስከትል ይችላል።

NWTND Newb Page 15-1.png
ህክምና

የሰውነት የፈሳሽ ማጠር ምልክት ሲታይ፣ ሕፃኑ ተቅማጥ ካለው ወይንም እያስታወከ ከሆነ ሕፃኑ እሺ እስካለ ድረስ በየ ሁለት ሰዓት ቶሎ ቶሎ እየቀሰቀሳችሁ አጥቡ። በተጨማሪ የፈሳሽ ማጠርን ለማስወገድ ውሀ ከትንሽ ጨው እና ከስኳር ጋር መስጠት ይቻላል። ይህን አይነት የፈሳሽ ማጠር ማስወገጃ ካጠባችሁ በኋላ ስጡ። አንዳንድ ጊዜ እናት በቂ ብታጠባም ሰውነትዋ በቂ ወተት ላይሰራ ይችላል (ስለዚህ በደንብ ለመረዳት ይህንን ተጫኑ)።

የሰውነት ፈሳሽ ያጠረው ሕፃኑ እየተሻለው ካልሄደ በትንሽ ሰዓት ውስጥ የልጁ ሰውነት ውስጥ በቂ ውሀ እንዲኖር የሚያስፈልገውን ለማድረግ አፋጣኝ ህክምና ፈልጉ።

መንደብደብ

አዲስ የተወለዱ ሕፃናት መንደብደብ፣ እንደ ጭርት የሚመስል፣ ወይንም የሰውነት ቀለማቸው ለየት ሊል ይችላል እንደዚህ አይነት ነገሮች በአብዛኛው ጊዜ ምንም ጉዳት የለውም እና ምንም ሳይደረግበት በራሱ ይድናል። የልጆች መቀመጫ ላይ መንደብደብ ብዙ ጊዜ የሚከሰተው በሽንት ወይንም በአይነ ምድር እርጥበት ነው ስለዚህ መቀመጫቸውን በየጊዜው አጽዱ። በተጨማሪም ጨርቃቸው/ ዳይፐራቸው እንደረጠበ ወይንም እንደቆሸሸ ቶሎ ቀይሩላቸው። ተለቅ ላለ ሕፃን ወይንም በሙቅ ቀናት መንደብደቡ እንዲሻለው መቀመጫቸውን አለመሸፈን እና ዚንክ ኦክሳይድ የሚባል ቅባት ሊረዳ ይችላል። በትንሽ ቀን ውስጥ ካልዳነ የይስት ኢንፌክሽን ሊሆን ይችላል። ለይስት ኢንፌክሽን ናይስታቲን ክሬም ( nystatin cream) ተጠቀሙ።

ሕፃኑ ውሀ የመቋጠር ወይንም ብዙ ቡጉር ካለው እና በተለይ ሕፃኑ የታመመ ከመሰለ ወይንም ራስ ምታት ካለው ኢንፌክሽን ሊኖረው ይችላል። ምንም የመሻል ምልክት ካልታየ ወይንም የኢንፌክሽኑ ምልክቶች እየባሱ ከሄዱ እዚህ የተጠቀሱትን አንቲባዮቲክ(antibiotics) ስጡ።

ቢጫ አይን

ቢጫ ዓይን ወይንም ቢጫ ቆዳ ጆንዲስ(jaundice) በሽታ ይባላል ለጠይም/ለጥቁር ሕፃኑ ዓይናቸውን መርምሩ። የጆንዲስ(jaundice) በሽታ ሕፃኑ በተወለደ ከሁለተኛ ቀን እስከ አምስተኛ ቀን ድረስ አደገኛ አይደለም። ለጆንዲስ(jaundice) በሽታ ጠቃሚ ህክምና ወይንም እንክብካቤ ጡት ቶሎ ቶሎ ማጥባት ነው። ቶሎ ቶሎ ማጥባት የሕፃኑን ዓይን ቢጫ ያደረገውን ኬሜካል ከሕፃኑ ሰውነት ውስጥ እንዲወጣ ይረዳል። ለማጥባት በየ ሁለት ሰዓት ሕፃኑን ቀስቅሱ በተጨማሪ ሕፃኑን አስራ አምስት ደቂቃ ያህል ራቁትዋን/ራቁቱን አርጎ የተወሰነ ጊዜ በቀን ውስጥ የፀሐይ ብርሀን እንዲያገኝ ማድረግ ይረዳል።

አስጊ ምልክቶች
 • ጆንዲስ(jaundice) በሽታ ወድያውኑ ይጀምራል-ሕፃኑ በተወለደች በ24 ሰዓት ውስጥ
 • ጆንዲስ(jaundice) በሽታ ቆየት ብሎ ሲጀምርና አጠቃላይ ሰውነትን ሲሸፍን
 • ጆንዲስ(jaundice) በሽታ የያዛት ሕፃን በሀይል እንቅልፍ እንደያዛት ስትሆን ወይንም ለመመገብ ሕፃንዋን መቀስቀስ ከባድ ነው

ከነዚህ ምልክቶች አንዱ ከታዩ አፋጣኝ እርዳታ ፈልጉ

ዓይን

አይን አር ያለው አይን

ዓይን እንባ እና ቅባት እንዲያገኝ የሚረዱት ትንንሽ የዓይን ቀዳዳዎች ሊደፈኑ እና ዓይን አር አይነት ነገር ሊከማች ይችላል። በንጹህ ሞቅ ባለ እርጥብ ጨርቅ አጽዱት ስታጸዱ የተለያየ ንጹህ ጨርቅ ተጠቀሙ ምክንያቱም አንዱ ዓይን ኢንፌክሽን ካለ ሌላው አይን ላይ እንዳይተላለፍ።

ብዙ ሴቶች ክለሚዲያ ወይንም ጎነሪያ ቢኖራቸዎም በሽታው እንዳላቸው አያቁም። ከወሊድ በኀላ ወድያውኑ አንቲባዮቲክ ለአይን መሰጠት ከናት ወደ ልጅ የተላለፈው ጎነርያ የአይን ችግር እንዳያመጣ ይረዳል።

ሕፃን ከተወለደ ከ5 ቀን በኋላ ደም ያለው ዓይን አር፣ቀይ ከሆነ እና ካበጠ የዓይን ሽፋን ጋር ከታየ ሕፃንዋ/ሕፃኑ ክላሚድያ ወይንም ጎነሪያ(gonorrhea) የተባለው በሽታ ይዟት ይሆናል። ስለዚህ ህክምናው ለክለሚዲያው በአፍኢራይትሮሚሲን(erythromycin) የተባለውን መድኃኒት ፈጭታችሁ ከእናት ጡት ወተት ጋር በመደባልቃችሁ ለሕፃኑ/ንዋ በመስጠት ነው። የትኛው በሽታ ህመሙን እንዳመጣ መመርመር ካልተቻለ ወይንም ካልታወቀ የሁለቱንም ህክምና/መድኀኒት ስጡ(26ተኛ ገጽ እዩ)። ክለሚድያ ወይንም ጎነሪያ(gonorrhea) የተባለው በሽታ ሕፃንዋ/ሕፃኑ ካላት/ካለው የአባለዘር በሽታ ስለሆነ እናትዋ እና አባትዋ መታከም ይኖርባቸዋል።የብልት ችግሮች እና ኢንፌክሽኖች ለመረዳት ይህንን ጎብኙ(እየተቀናጀ ነው)። የዓይን ኢንፌክሽን በአንድ ወይንም ሁለት ቀን ውስጥ ካልዳነ ሌላ አንቲባዮቲክ(antibiotics) ሕፃንዋ/ሕፃኑ እንዳትታወር/እንዳይታወር ያስፈልጋል ስለዚህ አፋጣኝ እርዳታ ፈልጉ።

ለስላሳው ቦታ

የሕፃኑ ጭንቅላት ላይ ያለው ለስላሳው ቦታ ጠፍጣፋ መሆን አለበት። የሕፃን ጭንቅላት ላይ የጐደጐደ ወይንም ያበጠ ለስላሳው ቦታ የአደገኛ ነገር ምልክቶች ናቸው።

NWTND Newb Page 16-3.png
NWTND Newb Page 16-2.png
የጐደጐደ ለስላሳው ቦታ የሰውነት ፈሳሽ ማነስ ምልክት ነው። በተደጋጋሚ ሕፃንን አጥቡ እና የሰውነት ፈሳሽን ለመጨመር የሚረዳን ፈሳሽ ስጡ ያበጠ ለስላሳው ቦታ የመንጋጋ ቆልፍ(meningitis) ምልክት ነው። አንቲባዮቲክ(antibiotics) ስጡ

እትብት

እትብቱ ከተቆረጠ በኋላ የቀረውን ትርፍ እትብት አትነካኩት ወይንም አትሸፍኑ። የሽንት ጨርቅ እና ዳይፐር እንዳይነካው። ላለመንካት ሞክሩ መንካት ካለባችሁ በሳሙና እና በውሀ እጃችሁን ታጠቡ።እንብርቱ ወይንም አካባቢው ከቆሸሸ ወይንም የደረቀ ደም ካለ በሳሙ እና በውሀ በንጹሕ ጨርቅ አጽዱ። እናት እንብርቱን ከሸፈነች በንጹሕ ጨርቅ ይሁን፣አይጥበቅ እና በቀን ውስጥ በተጋጋሚ ጨርቁን ቀይሩ።

NWTND Newb Page 17-1.png
የሕፃንን እትብት አትነካኩ ይህንን ማረግ ኢንፌክሽን እንዳይኖር ይረዳል

ከአንድ ሳምንት በኋላ እትብቱ ደርቆ ይወድቃልእትብት አካባቢው ቀይ ከሆነ፣መጥፎ ከሸተተ፣ ወይንም መግል ካለው ኢንፌክሽን ይዟል ማለት ነው። በደንብ አጽዱት እና ለሕፃንዋ አሞክሲሊን(amoxicillin) ስጡ። የሕፃንዋ ፊት ከተለመደው ውጭ ቆጣ ወይንም ቀየር ካለ፣መጥባት ካልቻለች፣ወይንም የሕፃንዋ/የሕፃኑ ሰውነት ጭንቅ ያለ ከመሰለ፣ እና በተጨማሪ ኢንፌክሽን እትብቱ አካባቢ ካለ ቲታነስ ሕፃኑትዋ ይዟት ይሆናል (እየተቀናጀ ነው)ይህ በጣም አስጊ እና አፋጣኝ ጉዳይ ነው። የመጀመርያ እርዳታ