Hesperian Health Guides

ምዕራፍ 27: አራስ፡እና፡ጡት፡ማጥባት

የጤና ዊኪ > አዲሱ ሐኪም በሌለበት > ምዕራፍ 27: አራስ፡እና፡ጡት፡ማጥባት

ይህ ምእራፍ ውስጥ፦

ከወሊድ፡በኋላ፡መደረግ፡ያለባቸው፡ እንክብካቤዎች

ልክ፡ከወሊድ፡በኋላ፡ባለው፡ሰዓታት፡ውስጥ፡የአራስን፡ልጅ፡ ሕይወት፡እና፡ጤና፡ለረጅም፡ጊዜ፡ለመጠበቅ፡የሚቀጥሉትን፡ነገሮች፡አድርጉ፦

 1. አራስዋ፡ልጅ፡እየተነፈሰች:እንደሆነ:አረጋግጡ
 2. 2. አራስዋን፡ልጅ፡በደንብ፡አድርቋት፡እና፡ከእናትዋ፡ሰውነት፡ጋር፡በማስጠጋት፡ እንዲሞቃት፡አድርጉ
 3. ጡት፡መጥባት፡እንድትለምድ፡አድርጉ

አራስዋ፡ልጅ፡እየተነፈሰች፡ነው?

ልጅትዋ፡ስትወለድ፡በደንብ፡አድርቃችሁ፡ወደ፡እናትዋ፡ጡት፡ስታስጠጉዋት፡አራስዋ፡እየተነፈሰች፡እንደሆነ፡አረጋግጡ።ምክንያቱም፡አራስዋ፡ ልጅ፡ካልተነፈሰች፡በአፋጣኝ፡አንዳንድ፡ነገሮችን፡በማድረግ፡ሕይወትዋን፡ማዳን፡ይቻላል።

NWTND Newb Page 1-1.png
ጠንካራ፡እግሮች፡እና፡እጆች
ጥሩ፡ቀለም፡ያላት

የምትተነፍስ፡ወይንም፡ የምታለቅስ
NWTND Newb Page 1-2.png
የዛለ፡እና፡ውድቅ፡ያለ፡ሰውነት
ያልተለመደ፡ የሰውነት፡ቀለም፣እና፡ጠጃማ፡ የሆነ፡ሰውነት

ለመተንፈስ፡የሚታገል፡ አራስ፡ልጅ፣የማይተነፍስ፣እና፡ የማያለቅስ፡ወይንም፡ድምጽ፡ የማያሰማ
የላይኛው፡ስእል፡ላይ፡ያለችው፡አራስ፡ጤናማ፡ትመስላለች መግለጫ፦የላይኛው፡ስእል፡ላይ፡ያለው፡አራስ፡አፋጣኝ፡ እርዳታ፡ያስፈልገዋል

አራስዋ፡ልጅ፡የዛለ፡ሰውነት፣ያልተለመደ፡የሰውነት፡ቀለም፣ወይንም፡የማትተነፍስ፡ከሆነ፦

ልጅትዋን፡እንዳትመትዋት

 1. በቀስታ፡ከአራስዋ፡ልጅ፡አፍ፡ውስጥ፡ያለውን፡አክታ፡በንጹሕ፡ጨርቅ፡በተጠቀለለ፡ጣት፡አጽዱ። በህክምና፡ማጽጃ፡ስርንጅ፡ወይንም፡መሳቢያ፡አክታ፡ከአራስዋን፡ልጅ፡አፍ፡አውጡ፡እና፡ንፍጥ፡ከአራስዋ፡አፍንጫ፡ዉስጥ፡ማዉጣት፡ይቻላል።
 2. የላይኛው፡ስዕል:
  NWTND Newb Page 2-2.png
 3. በደንብ፡የአራስዋን፡ልጅ፡ጀርባ፡ወደ፡ላይ፡እና፡ወደታች፡እሹ፡፡በዚውም፡በፎጣ፡ ሰውነትዋን፡አድርቋት፡እና፡እንዲሞቃት፡አድርጉ፣በተጨማሪ፡የታችኛውን፡እግርዋን፡ እሹ።ይህንን፡ነገሮች፡ማድረግ፡የአራስዋን፡ልጅ፡ሰውነትዋን፡ጥሩ፡ትንፋሽ፡ እንድትወስድ፡ያበረታታል፡፡

  አራስዋ፡ልጅ፡የማትተነፍስ፡ከሆነ፡ወይንም፡መተንፈስ፡ ካቆመች፡አዳኝ፡ትንፋሽ፡መስጠት፡ያስፈልጋል፡፡


አዳኝ፡ትንፋሽ፡አሰጣጥ

1.አራስዋን፡ልጅ፡ጠንከር፡ያለ፡ነገር፡ላይ፡እንደ፡መሬት፡ወይንም፡ጠረቤዛ፡ላይ፡አስተኙዋት፦ጠንከር፡ያለ፡ነገር፡ላይ፡ስታስተኝዋት፡ እንዳይበርዳት፡ከታች፡ጨርቅ፡መኖሩን፡እና፡ትንሽም፡ከላይ፡እንደተሸፈነች፡አረጋግጡ፡፡
2.የአራስዋን፡ልጅ፡አገጭ፡ትንሽ፡ከፍ፡አርጉ፦አገጭዋ፡ትንሽ፡ወደ፡ሰማይ/ጣሪያ፡ከፍ፡እንዲል፡፡ትንሽ፡የተጠቀለለ፡ጨርቅ፡ከትከሻዋ፡ ስር፡ማረግ፡ጉሮሮዋን፡ክፍት፡እንዲሆን፡ይረዳል።
illustration of the above: baby with chin tilted up.
baby with chin touching her chest.
የአራስዋን፡ልጅ፡አገጭ፡ወደ፡ሰማይ/ጣሪያ፡እንደዚህ፡ከፍ፡ማለት፡አለበት. እንደዚህ፡አይደለም
3. አፋችሁን፡በደንብ፡ክፈቱና፡የአራስዋን፡አፍ፡እና፡አፍንጫ፡በአፋችሁ፡ዙሪያውን፡ግጠሙ
a baby's face, showing the area to cover with your lips.
ስእሉ፡ላይ፡የሚታየውን፡ክብ፡ቦታውን፡በአፋችሁ፡በደንብ፡ሸፍኑ
የኦክሲጅን፡ሽፋን(ማስክ)፡ከአፍ፡ሌላ፡ሽፋን፡ ወይንም፡ከረጢት/ማስክ፡መጠቀም፡ይቻላል
4. ትንሽ፡ትንሽ፡ትንፋሽ፡አራስዋ፡ልጅ፡ውስጥ፡ክተቱ፦ትንሽ፡ትንሽ፡ፈጠን፡ያለ፡ትንፋሾች፡በየ1፡ወይንም፡በየ2፡ሰከንድ፡ስጥዋት።በሐይል፡ ተንፍሳችሁ፡ትንሽ፡ሳንባዋን፡እንዳትጎዱ፡ተጠንቀቁ።
በየትንፋሽ፡መሀል፡በሀሳብዋ፡እየቆጠረች፡ያለች፡ሰትዮ
1 ....
ትንሽ፡እፍታ፡ትንፋሽ፡እየተነፈሰች፡እያሰበች፡ያለች፡ሰትዮ
ተንፍሽ


አየር፡እማይገባ፡ከመሰላችሁ፡ወይንም፡እማይገባ፡ከሆነ፡ጉሮሮዋ፡ክፍት፡እንደሆነ፡ለማረጋገጥ፡የልጅትዋን፡አገጭ፡ትንሽ፡ወደ፡ላይ፡ከፍ፡ አርጉ።ከዛ፡በድጋሚ፡ሞክሩ

አራስዋ፡ልጅ፡ማልቀስ፡ከጀመረች፡ወይንም፡በራስዋ፡30፡ትንፋሽ፡በየደቂቃ፡ከተነፈሰች፡ለአሁን፡ደህና፡ናት፡ማለት፡ነው።እናትዋ፡ደረት፡ ላይ፡አርጋችሁ፡እንደሚሞቃት፡አድርጉ።ከዚህ፡በኋላ፡ደህና፡እንደምትሆን፡ቢገመትም፡ለሚቀጥሉት፡ሰዓታት፡በደንብ፡ተከታተልዋት። የአራስዋ፡ልጅ፡ሰውነት፡ቀለም፡ደህና፡ነው?ሳትቸገር፡እየተነፈሰች፡ነው?አፍዋ፡አካባቢ፡ወይንም፡ሰውነትዋ፡በጣም፡ከጠቆረ፡ወይንም፡ ያልተለመደ፡ቀለም፡ከሆነ፡አፈጣኝ፡እርዳታ፡ፈልጉ።

ከ20፡ደቂቃ፡ትንፈሽ፡እርዳታ፡በኋላ፡አራስዋ፡ልጅ፡በራስዋ፡መተንፈስ፡ካልጀመረች፡ልትሞት፡ትችላለች፡ስለዚህ፡ቤተሰቦችዋ፡ በጭንቀታቸው፡እና፡በሀዘናቸው፡ግዜ፡ድጋፍ፡ስለሚያስፈልጋቸው፡አካባቢቸው፡ሁኑ፡።

አራስዋን፡ሙቅ፡መሆንዋን፡አረጋግጡ፡እናትዋ፡ሰውነት፡ላይ


የአራስዋን፡ሰውነት፡ከናትዋ፡ ሰውነት፡ጋር፡አነካክታችሁ፡ የናት፡ደረት፡ላይ፡አድርጓት የአራስዋ፡ልጅ፡ጭንቅላት፡ላይ፡የሚያመለክተው፡ ቀስት፡እላይ፦የልጅትዋን፡ጭንቅላት፡በኮፍያ፡ ወይንም፡በብርድ፡ልብስ፡ሸፍኑ
አራስ፡ከናት፡ደረት፡ላይ፡በብርድ፡ልብስ፡ተሸፍና

ከአናት፡ጋር፡ከመሆን፡የበለጠ፡ነገር፡ለአራስ፡ልጅ፡የለም

አራስ፡ልጅ፡እንዲሞቀው፡እና፡ደረቅ፡እንዲሆን፡መደረግ፡አለበት።የአናት፡ሰውነት፡አራስን፡የልጅ፡ያሞቃል።አራስን፡ከአናት፡ ለማጠብ፡ወይንም፡ለመመርመር፡እንዳትለያዩ።አራስን፡ልጅ፡ወድያውኑ፡ማጠብ፡አያስፈልግም፡ደግሞም፡ወድያውኑ፡አራስን፡ ማጠብ፡በአደገኛ፡ሁኔታ፡አራስን፡ሊያቀዘቅዝ፡ይችላል።አራስን፡እና፡እናትን፡አዳኝ፡ትንፋሽ፡ለመስጠት፡ካልሆነ፡መለያየት፡አያስፈልግም።

 • አራስን፡ልጅን፡እናት፡ላይ፡ለማስቀመጥ፡አደራርቁ።
 • አራስዋን፡ለማሞቅ፡ራቁትዋን፡እናትዋ፡ደረት፡ላይ፡አድርጓት።ከዚያም፡በኋላ፡እናትዋን፡እና፡ልጅትዋን፡በብርድ፡ልብስ፡ ወይንም፡በጨርቅ፡ሸፍኑ።በአስቸኮይ፡አራስዋ፡ልጅ፡እንዳይቀዘቅዛት፡እርጥብ፡ብርድ፡ልብስ፡ቀይሩ።


እናት፡ሆስፒታል፡መሄድ፡ካለባት፡ወይንም፡በሌላ፡ምክንያት፡ልጅዋን፡መያዝ፡ካልቻለች፡ወድያውኑ፡አባት፡ወይንም፡ሌላ፡ቤተሰብ፡ በሰውነት፡አቅፈው፡ሊይዟት፡ይችላሉ።

እናት፡አራስ፡ልጅዋን፡ደረትዋ፡ላይ፡አድርጋ፡በልብስዋ፡ሸፍና

ጡት፡ማጥባት፡ጀምሩ

አራስ፡ልጆች፡በተወለዱ፡በአንድ፡ሰአት፡ውስጥ፡እንቅልፍ፡ስለሚወስዳቸው፡ ከመተኛታቸው፡በፊት፡ጡት፡ማጥባት፡ያስፈልጋል፡፡ስለዚህ፡አራስዋ፡ልጅ፡ወድያውኑ፡ ካልጠባች፡ትንሽ፡ጡትን፡ጨመቅ፡በማድረግ፡የተወሰነ፡ጠብታ፡አፍዋ፡ላይ፡አርጎ፡አራስዋ፡ መጥባት፡እንዲያምራት፡ወይንም፡የአራስዋን፡ጉንጭ፡በጡቱ፡ጫፍ፡ኮርኮር፡አርጉ፡ ምክንያቱም፡ለአራስዋ፡ልጅ፡እንደ፡ጡት፡ወተት፡ጠቃሚ፡ነገር፡የለም።በተጨማሪ፡ የመጀመሪያ፡የጡት፡ወተት፡(ካሎስትሮም)፡አስፈላጊነትን፡እና፡ጥቅምን፡ በደንብ፡ለመረዳት፡የሚከተለውን፡ሊንክ፡ተጫኑ።