Hesperian Health Guides
አራስ፡እና፡ጡት፡ማጥባት: መድኀኒቶች
ማውጫ
አንቲባዮቲክ (antibiotics) ኢንፌክሽንን ይከላከላል
አምፒሲሊን(Ampicillin) እና አሞክስሊን(amoxicillin)፦
አምፒሲሊን(Ampicillin) እና አሞክሲሊን(amoxicillin) ለየት ያሉ አንቲባዮቲክ(antibiotics) አይነቶቾ በመሆናቸው ብዙ አይነት ባክቴሪያዎችን ይገላሉ ። ብዙ ጊዜ አምፒሲሊን(Ampicillin) ወይንም አሞክስሊን ሲታዘዝ አንዱ ሌላኛውን መተካት ይቻላል በትክክለለኛ መጠን ከተሰጠ(እታች እዩ በዝርዝ ለመረዳት)።
የሕፃናት እና የልጆች ጤና ለመጠበቅ አምፒሲሊን(Ampicillin) እና አሞክስሊን ጠቃሚ ናቸው በተጨማሪ አደገኝነት የላቸውም። ለጆሮ እና ለሳንባ ምች ህክምና ጠቃሚ ናቸው። በተጨማሪ አምፒሲሊን(ampicillin) መንጋጋ ቆልፍን(meningitis) እና ሌላ ሀይለኛ ኢንፌክሽንን ለማከም ጠቃሚ ነው።
እነዚህ ሁለት መድሐኒቶች በተለይ አሞክሲሊን(amoxicillin) ማጥወልወል እና ተቅማጥ ሊያስከትሉ ይችላሉ። ስለዚህ ልጆች ተቅማጥ ካላቸው ሌላ አይነት አንቲባዮቲክ(antibiotics) መስጠት የተመረጠ ነው። ሕፃኑ ለአንፒሲሊን አለርጂ ከሆነ ብዙ ጊዜ የሚታየው መንደብደብ ነው። በትንሽ ሰዓት ውስጥ የሚመጣ እና የሚሄድ መንደብደብ የአለርጂ ምልክት ነው። ይህን ምልክት ካያችሁ ወድያውኑ መድኋኒቱን ለሕፃኑ መስጠት አቁሙ እና በድጋሚ ፔኒሲሊን(penicillin) እንዳትሰጡ ምክንያቱም የወደፊት አለርጂ ሐይለኛ ወይንም ለህይወት አስጊ ሊሆን ይችላል። ለአንዳንድ ችግሮች ኢራይትሮሚሲንን(erythromycin) መጠቀም ይቻላል። እንደ ኩፍኝ አይነት መንደብደብ በአብዛኛውን ጊዜ መድኀኒቱ ከተጀመረ ከሳምንት በኋላ የሚጀምር እና ለመጥፋት ቀናት የሚወስድ መንደብደብ አለርጂ ላይሆን ቢችልም አለርጂ ይሁን አይሁን ለማወቅ ከባድ ስለሆነ መድሐኒቱን መስጠት ማቅዋረጥ በአብዛኛውን ጊዜ የተመረጠ ነው።
አንዳንድ ቦታ በሽታዎች ጠንክረው ይህንን አይነት መድሐኒቶችን መቋቋም ጀምረዋል ስለዚህ እንዳላችሁበት ቦታ ሁኔታ መድሐኒቶቹ አንዳንድ በሽታዎችን (እንደ ስታፓይሎከስ(staphylococcus)፣ሺጌላ(shigella) ወይንም ሌላ ኢንፌክሽንን) ለማዳን አይችሉ ይሆናል።
አምፒሲሊን(Ampicillin) እና አሞክሲሊን(amoxicillin) በአፍ ሲወሰዱ በደንብ ይሰራሉ። መድሐኒቱን ለመስጠት ሰባብሩት ወይንም የመድሐኒቱን ዱቄት አውጥታችሁ የሚያስፈልገው ያህልን ውሰዱና ከትንሽ የጡት ወተት ጋር ቀላቅሉ። በብርጭቆ ወይንም በማንክያ ወተቱን እና መድሐኒቱን ለሕፃኑ መግቡ። አምፒሲሊን(Ampicillin) በመርፌ ሊሰጥ ይችላል ግን ለኃይለኛ በሽታዎች እንደ መንጋጋ ቆልፍ(meningitis)፣ የታመመው ሰው ሲያስታውክ ወይንም መዋጥ ሲያቅተው ቢሆን የተመረጠ ነው።
አንቲባዮቲክ(antibiotics) ሲሆን አንዴ መድኃኒቱ መሰጠት ከተጀመረ ሳይቋረጥ እዚህ በተጠቀሰው መሰረት ለአጭር ቀናት/ጊዜ ያህል ቢያንስ መሰጠት አለበት የኢንፌክሽን ምልክት ከቀጠለ መድኃኒቱን መውሰድ መቀጠል ያሰው አለበት የኢንፌክሽን ምልክት ለ24 ሰዓት እስኪጠፋ። የኢንፌክሽን ምልክት ከቀጠለ ኢንፌክሽን የያዘው ሰው መድኋኒቱን በትክክል እየወሰደ እና መድኃኒቱ የሚሰጥበትን የመጨረሻ ረጅም ቀን ካሟላ መድኃኒቱን መውሰድ ማቆም እና የህክምና እርዳታ መፈለግ ያስፈልጋል። ኤች አይቪ(HIV) ላለው ሰው መድኃኒቱ መሰጠት ለሚቻልበት ረጅም ቀናት ያህል ስጡ። በተጨማሪም ምን ያህል አንቲባዮቲክ መሰጠት እንዳለበት የሚሰጠው ሰው እድሜ ኪሎ እና የኢንፌክሽኑ ሁኔታ ይወስነዋል። በአጠቃላይ አነስተኛ ዶዝ ለቀጭን ሰው ወይንም አነስተኛ አለርጂክ ላለው ስጡ በተቃራኒ ደግሞ ኀይለኛ ዶዝ ወፈር ላለ ሰው ወይንም በጣም ኀይለኛ አለርጂክ ላለው ስጡ።
አሞክሲሊን (AMOXICILLIN)ለአብዛኛው ሕፃን ኢንፌክሽኖች
¼ የ250 ሚሊግራም ኪኒን ወይንሞ
½ የሻይ ማንክያ (1.25 ሚሊ ሊትር) የ125 ሚሊግራም/5 ሚሊ ሊትር ሲሮፕ ወይንሞ
¼ የሻይ ማንክያ (2.5 ሚሊ ሊትር) የ250 ሚሊግራም/5 ሚሊ ሊትር ሲሮፕ
ለአብዛኛው አራስ ኢንፌክሽኖች
½ የ250 ሚሊግራም ኪኒን ወይንሞ
1 የሻርባ ማንክያ (5 ሚሊ ሊትር) የ125 ሚሊግራም/5 ሚሊ ሊትር ሲሮፕ
ለኀይለኛ ኢንፌክሽን አራስ ሕፃኑ ላይ እንደ መንጋጋ ቆልፍ(meningitis)
የታፋ ጡንቻ ላይ በመርፌ ስጡ። መርፌ እንዴት እንደሚሰጥ በዝርዝር ለመረዳት መድኃኒት፣ምርመራ፣ እና ህክምናን እዩ (በመቀናበር ላይ ነው)።
500 ሚሊግራም አምፒሲሊንን(Ampicillin) ከ2.1 ሚሊ ሊትር ውሀ ጋር ቀላቅሉ። ይህ የ500 ሚሊግራም ካንሰንትሬሽን በየ 2.5 ሚሊ ሊትር ይሰራል።
ያልተቀላቀለ የ2 ሚሊ ሊትር ጀንታሚሲን(gentamicin) ቫያል 40 ሚሊግራም በየ ሊትሩ።
ጀንታሚሲን(gentamicin) በጣም ጠንካራ አምኒግሎካሳይድ (aminoglycoside) የአንቲባዮቲክ ቤተሰብ ነው። ጀንታሚሲን(gentamicin) በትክክል መጠኑ(ዶዙ) መሰጠት አለበት በስህተት በዛ ያለ ከተሰጠ የኩላሊት ጉዳት ወይንም የጆሮ መደንቆር ሊያስከስትል ይችላል። በመርፌ ወይንም በአይቪ ብቻ ነው መሰጠት ያለበት(በደምስር/በቬይን)። ስለዚህ በኢመርጀንሲ ጊዜ ወደ ህክምና እርዳታ ሲኬድ ብቻ መጠቀም የተመረጠ ነው። ልጅ ዲሀይድሬትድ ወይንም የውኃ ማጠር ምልክት ካሳየ/ች የጡት ወተት እና የዲኃይድሬሽን ፈሳሽ ቶሎ ስጡ።
ከአንድ ሳምንት በታች ለሆነ ሕፃንኢራይትሮሚሲን(Erythromycin)
ኢራይትሮሚሲንም(erythromycin) ልክ እንደ ፔኒሲሊን(penicillin) አብዛኛው ኢንፌክሽኖችንን ያድናል በተጨማሪ ፔኒሲሊን አለርጂክ ለሆኑ ሰዎች መጠቀም ይቻላል። ለአብዛኛውን ኢንፌክሽኖች በቴትራሳይክሊን ምትክ መጠቀም ይቻላል። ኢራይትሮሚሲን(erythromycin) አሁን በአለም ዙሪያ የሳንባ ምችን(pneumonia) ለማዳን ከፔኒሲሊን(penicillin) የተሻለ ይሰራል። በተጨማሪ ለዲፍቴርያ(diphtheria) እና ለፔርቱሲስን(pertussis)/ኀይለኛ ማስነጠስ(whooping cough) መጠቀም ይቻላል። መድሐኒቱ ሊያመጣ
ኢራይትሮሚሲን(erythromycin) ማጥወልወል እና ተቅማጥ ሊያመጡ ይችላሉ በተለይ ልጆች ላይ። ከ2 ሳምንት በላይ አትጠቀሙ ጆንዲስ(jaundice) ሊያመጣ ስለሚችል።
ሴፍትሪአክሳን(Ceftriaxone)
ሴፍትሪአክሳን(ceftriaxone) የሴፍሓሎስፖሪን ቤተሰብ ነው። ሴፍሓሎስፖሪን ብዙ ባክቴሪያዎች ላይ የሚሰራ አንቲባዮቲክ ነው። ብዙ ጊዜ ውድ እና በቀላሉ ሁሉ ቦታ የሚገኝ አይደለም። ነገር ግን ብዙ ጊዜ አነስተኛ አደጋ እና ጉዳቶች ያለው መድኃኒት ነው ከሌላ አንቲባቲኮች ጋር ሲነጻጸር በተጨማሪም ኀይለኛ በሽታዎችን እንደ ሴፕሲስ(sepsis) መንጋጋ ቆልፍ(meningitis) እና ፔኒሲሊንን ለተቋቋሙ ኢንፌክሽኖች ን ለማከም ጠቃሚ ነው። አካባቢያቾሁ ለተመከረው ኢንፌክሽን ብቻ በመጠቀም ይህ መድኃኒትን ሰውነት እንዳይቋቋመው እና ጠቃሚነቱ እንዲቀጥል ይረዳል። ሴፍትሪአክሳን(ceftriaxone) በተለይ ለጎነሪያ(gonorrhea) በሽታ በጣም ጠቃሚ ሲሆን በተጨማሪ ለህጻናት አይን ጎነሪያ(gonorrhea) ኢንፌክሽን ጠቃሚ ነው። ከዛ ውጭ ግን ለአዲስ ለተወለዱ ከ1 ሳምንት በታች ለሆኑ ህጻናት መሰጠት የለበትም እና ከ1ወር በታች ከሆኑ ህፃናት አካባቢ በተቻለ ማስወገድ ይለረጣል።
ከአንድ ሳምንት በታች ለሆነ ሕፃን ሴፍትሪአክሳን(ceftriaxone) አትስጡ። በተጨማሪ ከቀናቸው በፊት ለተወለዱ ልጆች ወይንም ለትንንሽ ለሆኑ ልጆች አለመስጠት የተመረጠ ነው (በተለይ ከጊዜያቸው በፊት የተወለዱ ከመሰሉ)። ጆንዲስ(jaundice) ካላቸው መድመኒቱን እንዳትለጡ።
ሴፍትሪአክሳን(ceftriaxone) በመርፌ የታፋ ጡንቻ ላይ በመከተብ ወይንም በአይቪ (በደምስር) ብቻ ነው የሚሰጠው። ክትባቱ በጣም ሊያም ይችላል። እንዴት እንደሚደረግ ካወቃችሁ ከ1% ኢንዶኬይን ጋር ቀላቅሉ።
ጎነሪያ(gonorrhea) አይን ኢንፌክሽን ለያዛቸው 7 ቀን በላይ ለሆናቸው አራሶችማለትም፦ ለ3ኪሎ ግራም አራስ 225 ሚሊ ግራም በቀን አንዴ በመርፌ ስጡ
ከፍ ላለ ለ6ኪሎ ግራም ሕፃን 450 ሚሊ ግራም በቀን አንዴ በመርፌ ስጡ