Hesperian Health Guides

ከወሊድ፡በኋላ፡ያሉት፡ሰዓታት

የጤና ዊኪ > አዲሱ ሐኪም በሌለበት > ከወሊድ፡በኋላ፡ያሉት፡ሰዓታት

ከወሊድ፡አንድ፡ወይንም፡ሁለት፡ሰዓት፡በኋላ፡አራስዋ፡ልጅ፡ጡት፡ከጠባች፡እና፡እናትዋ፡ደህና፡ እንደሆነች፡ካረጋገጣችሁ፡ለአራስዋ፡መሰጠት፡ያለበትን፡መድሐኒቶችን፡ስጡ።ከዛም፡ቀስ፡ ብላችሁ፡አራስዋን፡ከራስ፡እስከ፡እግር፡ጣትዋ፡ደህና፡እንደሆነች፡መርምሩ/አረጋግጡ፡ አራስዋን፡ስትመረምሩ፡እንዳይበርዳት፡ተጠንቀቁ።

መድኀኒቶች፡ለአራስ፡ልጅ

እናትየዋ፡ጎነሪያ፡ወይንም፡ክላይሚዲያ፡የአባለዘር፡በሽታ፡ካላት፡አራስዋ፡ስትወለድ፡ በሽታው፡ተላልፎ፡ሀይለኛ፡የዓይን፡በሽታ፡ሊይዛት፡ወይንም፡ለመታወር፡ሊያጋልጣት ፡ይችላል።እናቶች፡አባለዘር፡በሽታ፡እንዳላቸው፡አለማወቅ፡የተለመደ፡ክስተት፡ስለሆነ፡ ወንዱም፡ሆነ፡ሴትዋም፡በመመርመርና፡ለአባለዘር፡በሽታ፡የሚያስፈልገውን፡ህክምና፡ በመውሰድ፡በወሊድ፡ጊዜ፡የአባለዘሩ፡በሽታ፡ወደ፡አራስዋ፡አይን፡እንዳይተላለፍ፡ይረዳል። ስለ፡በሽታው፡ምልክቶች፡እና፡እንዴት፡መታከም፡እንዳለበት፡ለማወቅ፡የብልት፡ችግሮች ፡እና፡ኢንፌክሽን፡ተመልከቱ። የሴት፡አባለተውሊድ፡ችግሮች፡እና፡በሽታዎች (በመቀናበር ላይ ነው). አራስዋ፡በተወለደች፡አንድ፡ወይንም፡ሁለት፡ሰዓት፡ውስጥ፡ጎነሪያ፡የአባለዘር፡በሽታን፡መያዝ፡ለማስወገድ ፡ትንሽ፡እራይትሮማሲን (erythromycin) ፡ወይንም፡ቴትራሳይክሊን፡ቅባት፡ (tetracycline ointment) የአራስዋ፡ሁለቱም፡ዓይን፡ውስጥ፡ጨምሩ።ሄፒታይተስ፡ቢ (hepatitisB) (በመቀናበር ላይ ነው) ፡ወይንም፡የጨጓራ፡ካንሰር፡የበዛበት፡ቦታ፡የሄፒታይተስ፡ቢን፡ክትባት፡ለአራስዋ፡ልጅ፡መስጠት፡ጠቃሚ፡ነው።እናትየዋ፡ሄፒታይተስ ፡ቢ፡እንዳላት፡ካላወቀች፡በሽታው፡ወደ፡አራስዋ፡እንዳይተላለፍ፡ይህንን፡ክትባት፡መስጠት፡ይረዳል።እናቶች፡ሄፒታይተስ፡ቢ

፡እንዳላቸው፡አለማወቅ፡የተለመደ፡ነገር፡ነው።

አራስን፡ልጅን፡መመርመር

  • አራስዋ፡ልጅ፡ከሌሎች፡አራሳች፡ጋር፡ተመሳሳይ፡ናት፡ወይ?
  • በግራ፡በኩል፡ያሉት፡የሰውነት፡ክፍሎችዋ፡በቀኝ፡በኩል፡ካለው፡ጋር፡እኩል፣አንድ፡አይነት፣እና፡አንድ፡ቦታ፡ናቸው፡ወይ?
  • ቶዳዋ፡ጥሩ፡ነው?በተለይ፡በታችኛው፡ጀርባ፡ብዙ፡ጊዜ፡አፋጣኝ፡ሰርጀሪ፡የሚያስፈልገው፡ትንሽ፡ክፍተት፡ይገኛል።
  • ብልትዋ፡ደህና፡ነው? (ትንሽ፡እብጠት፡መጀመሪያ፡ቀን፡የሚያሰጋ፡አይደለም)
  • ሸንታለች?መጀመሪያ፡ቀን፡ላትሸና፡ትችላለች፡ግን፡የሚቀጥለው፡ቀን፡በዛ፡ያለ፡ጊዜ፡መሽናት፡አለባት።ከዚያም፡በየተወሰነ፡ሰዓት፡በደንብ፡ካልሸናች፣ሽንትዋ፡ከጠቆረ፣ወይንም፡ሀይለኛ፡ሽታ፡ካለው፡ተጨማሪ፡ጡት፡መጥባት፡አለባት።አለበለዚያ፡አንዳንዴ፡አለመሽናት፡አራስዋ፡ልጅ፡የኩላሊት፡ችግር፡እንዳላት፡ምልክት፡ነው።
  • አራስዋ፡ልጅ፡አይነ፡ምድር/ሰገራ፡ተቀምጣለች?ካልተቀመጠች፡ጉዋንቲ፡አርጋችሁ፡ትንሽ፡ጣታችሁን፡ፊንጢጣዋ፡ውስጥ ፡በመክተት፡ክፍተት፡እንዳለው፡አረጋግጡ።ክፍተት፡ከሌለ፡ኦፕራስዮን፡ያስፈልጋል።
NWTND Newb Page 6-1.png

አንዳንድ፡ለውጦች፡ምንም፡ጉዳት፡የላቸውም፡አንዳንድ፡ለውጦች፡ግን፡የአደገኛ፡ችግር፡ምልክት፡ሊሆኑ፡ይችላሉ።አንድ ፡ምልክት፡አራስዋ፡ልጅ፡ካላት፡ሌሎችም፡ችግሮች፡ሰውነቷ፡ውስጥ፡ሊኖሩ፡ይችላሉ።እነዚህ፡አራሳች፡ደህና፡እንደሚተነፍሱ ፣እንደሚሸኑ፣እና፡ቀለማቸው፡ደህና፡እንደሆነ፡በቅርብ፡ተከታተሉ።

የጭንቅላት፡ቅርጽ

የሕፃን፡ጭንቅላት፡እንደዚህ፡ሾል፡ማለት፡ወይም፡አበጥ፡ማለት፡የተለመደ፡ነገር፡ነው፡በተለይ፡ከረጅም፡ምጥ፡በኋላ።ሆኖም፡በተወሰነ፡ቀን፡ውስጥ፡እብጠቱ፡ይሆዳል።
illustration of the above: a baby's swollen head.
አንዳንድ፡አራስ፡ልጆች፡ጭንቅላታቸው፡ውስጥ፡መድማት፡ሊኖር፡ይችላል፦ይህ፡ሄማቶማ፡(hematoma)ይባላል።እነዚህ፡ባታዎች፡ስትጫኑ፡በጣም፡ስስ፡ነው።ሆኖም፡አደገኛ፡ነገሮች፡አይደሉም፡ግን፡እስኪጠፉ፡ወደ፡አንድ፡ወር፡በላይ፡ይወስ ድባቸዋል።
NWTND Newb Page 7-3.png
ያበጠ፡የአራስ፡ጭንቅላት

የተሰነጠቀ፡ከንፈር፡እና፡የተሰነጠቀ፡ላንቃ

 የተሰነጠቀ፡ከንፈር፡ያላት፡አራስ.

የተሰነጠቀ፡ከንፈርን፡ማየት፡ቀላል፡ሲሆን፡የተሰነጠቀ፡ላንቃን፡ግን፡ማየት፡ቀላል፡አይደለም።ስለልሆነ፡ላንቃዋ፡ዝግ፡መሆኑን፡ለማረጋገጥ፡ንጹህ፡ጣት፡አራስዋ፡ልጅ፡አፍ፡ውስጥ፡ከታችሁ፡ላንቃዋን፡ዳብሱ።የተሰነጠቀ፡ከንፈር፡ወይም፡የተሰነጠቀ፡ላንቃ፡ያላት፡አራስ፡ዋናው፡ችግሯ፡ጡት፡መጥባት፡ነው።

የተሰነጠቀ፡ከንፈር፡ያለውን፡አራስ፡ለማጥባት፡ስንጥቁን፡ቦታ፡በጣት፡ሸፍኑ።የተሰነጠቀ፡ላንቃ፡ያለውን፡አራስ፡ለማጥባት፡የጡቱን፡ጫፍ፡እና፡ዙሪያውን፡ወደ፡አንድ፡ወገን፡በኩል፡አራሱ፡አፍ፡ውስጥ፡ክተቱ።አሁንም፡አራሱ፡የመጥባት፡ችግር፡ካለው፡ጡት፡መጥባት፡እስኪችል፡በንጹህ፡ማንክያ፡ወይንም፡በጠብታ፡መስጭያ፡የጡት፡ወተቱን፡ስጡት።ጤናው፡ደህና፡እንዲቀጥል፡በተደጋጋሚ፡በደንብ፡መግቡት።የጡት፡ወተት፡በማንክያ፡ለመስጠት ፡በእጅ፡እንዴት፡ወተት፡እንደሚወጣ፡ለማወቅ፡የሚቀጥለውን፡ክሊክ፡አርጉ።.

የተሰነጠቀ፡ከንፈርን፡ከ3፡ወር፡በኋላ፡በሰርጀሪ፡ማስተካከል፡ሲቻል፡የተሰነጠቀ፡ላንቃ፡ደግሞ፡ከ1፡ዓመት፡በኋላ፡በሰርጀሪ፡ሊስተካከል፡ይችላል።እንደዚህ፡አይነት፡ሰርጀሪዎች፡ለሕጻናት፡ብዙ፡አገር፡በነጻ፡ስለሚሰጡ፡ክሊኒኮችን፡እና፡ሆስፒታሎቹን፡እንዳላቸው፡ጠያይቁ።

የተለያየ፡ዳሌ፣የዳሌ፡መጋጠሚያ፣እና፡ዳይስፕላዚያ

አንዳንድ፡አራሶች፡ሲወለዱ፡የተለያየ፡ዳሌ፡አላቸው፦እግራቸው፡ከዳሌያቸው፡መገናኛ፡ተንሸራቶ፡ወጥቶ፡ነው።ብዙ፡ጊዜ፡የተለያየው፡ዳሌ፡፡በጥቂት፡ቀን፡ወይንም፡በጥቂት፡ሳምንት፡ውስጥ፡እራሱ፡ይስተካከላል።

የአራስዋን፡እግር፡አጠፍ፡አርጋችሁ፡ጭንዋን፡እና፡የታችኛውን፡እግርዋን፡አንድ፡ላይ፡ያዝ፡አርጉና፡ጣታችሁን፡ዳሌዋ፡ላይ፡አርጉና፡አንድ፡በአንድ፡እግርዋን፡በቀስታ፡በክበብ፡አቅጣጫ፡ወደ፡ደጅ፡ወደ፡ታች፡እና፡ወደ፡ላይ፡አዙሩ፡ስዕሉ፡ላይ፡እንደሚታየው።አንድ፡እግር፡ቀደም፡ብሎ፡ከቆመ፣በድንገት፡ንቅንቅ፡ካለ፣ወይንም፡በድንገት፡ቋ፡ካለ፡ልክ፡ለማዞር፡ከፈት፡ስታረጉ፡ዳሌው፡ተለያይቷል፡ማለት፡ነው።
የላይኛው፡ስእል:የተለያየ፡ዳሌ፡ሲፈለግ
እናት፡ልጅዋን፡አዝላ፦አራስዋ፡ስትታዘል፡ስዕሉ፡ላይ፡እንደሚታየው፡የአራስዋ፡እግር፡እንደ፡ባላ፡ተደርጎ፡እንዲሆን
የአራስዋ፡እናት፡ልጅዋን፡ስታዝላት፡ስዕሉ፡ላይ፡እንደሚታየው፡የአራስዋ፡እግር፡እንደ፡ባላ፡ተደርጎ፡እንዲሆን።በሁለት፡ሳምንት፡አራስዋን፡ልጅ፡ስታዩ፡አሁንም፡እግርዋ፡ቀደም፡ብሎ፡ከቆመ፣በድንገት፡ንቅንቅ፡ካለ፣ወይንም፡በድንገት፡ቋ፡ካለ፡ተጨማሪ፡እርዳታ፡ፈልጉ። የአራስዋን፡እግር፡ክፍት፡አድረጎ፡ማዘል፡በጦሊት፡አራስዋን፡ልጅ፡ለተወሰነ፡ሳምንት፡ከረጅም፡ጊዜ፡የአካለ፡ስንኩል፡ችግር፡ለማዳን፡ሊረዳ፡የሚችል፡ነገር፡ነው።

ብራኬት፡እግር፡ያለው፡አራስ

የአራስ፡እግር፡ወደ፡ውስጥ፡ወይንም፡ትክክል፡ያልሆነ፡ዓይነት፡ቅርጽ፡ካለው፡ወደ፡ትክክል፡መሆን፡ወዳለበት፡አቅጣጫ፡አጠፍ፡ለማረግ፡ሞክሩ፡እና፡በቀላሉ፡መለስ፡ካለ፡በተደጋጋሚ፡በቀን፡ውስጥ፡ቦታው፡መለስ፡አርጉት።ይህንን፡መደጋገም፡የአራስ፡እግር፡ትክክል፡ቦታ፡እንዲውል፡ይረዳል።በቀላሉ፡መመለስ፡ካልተቻለ፡አራሱን፡ተወለደ፡ከትንሽ፡ቀን፡በኋላ፡ወደ፡ጤና፡ጣቢያ፡ውሰዱ።የአራሱ፡እግር፡ላይ፡ጄሶ፡መደረግ፡አለበት።ጄሶ፡በጥሩ፡ጊዜ፡ቶሎ፡ከተደረገ፡ሰርጀሪ፡ወይንም፡አካለ፡ስንኩል፡ከመሆን፡ያድናል።
ወደ፡ውስጥ፡የገባ፡እግር፡ያለው፡አራስ
ልጅ፡እግር፡ላይ፡ጄሶ፡ተጠቅልሎ

ትርፍ፡የእጅ፡ወይንም፡የእግር፡ጣት

ትርፍ፡የእጅ፡ወይንም፡የእግር፡ጣት፡ላይ፡አጥንት፡ከሌለ፡ክር፡ዙርያውን፡አጥብቆ፡በማሰር፡ትርፍ፡ጣቱ፡ደርቆ፡እንዲወድቅ ፡ማድረግ፡ይቻላል።ጣቱ፡አጥንት፡ካለው፡ወይንም፡ትልቅ፡ጣት፡ከሆነ፡ምንም፡ጉዳት፡ስለሌለው፡ትርፍ፡ጣቱን፡መተው፡ ይመረጣል። =እንደዚህ፡ስዕሉ፡ላይ፡እንደሚታየው፡ታች: ትርፍ፡ጣት፡በክር፡ዙሪያውን፡ተጠቅልሎ.

ስዕሉ፡ላይ፡እንደሚታየው፡የጣቶች፡ትንሽ፡መጠባበቅ፡ችግር፡የለውም

NWTND Newb Page 8-5.png

ከሁለት፡ጣቶች፡በላይ፡ጣቶች፡ከተጠባበቁ፡ጣቶች፡በደንብ፡እንዲሰሩ፡ሰርጀሪ፡ያስፈልጋል።

የወደሁዋላ፡በሽታ

የወደ ሁዋላ በሽታ ችግር ያለው ሕፃን ሲወለድ ወድያውኑ ወይንም ከትንሽ ጊዜ በሁዋላ ልጁ አደግ ሲል ሊታይ ይችላል። ይህ በሽታ የጭንቅላት ወደሁ ዋላነት ያመጣል። የወደሁዋላ በሽታ ችግር ያላቸው ልጆች የሚቀጥሉትን ምልክቶች ያሳያሉ:

NWTND Newb Page 9-1.png
ወደ ላይ ያለ አይን
ጠፍጣፋ ፊት
የእጅ መዳፍ ላይ አንድ መስመር
ትንሽ ጆሮ ከላዩ ላይ ትርፍ ስጋ ያለው
የክንዳቸው አጥንት መጋጠምያ በደንብ አይታይም
NWTND Newb Page 9-2.png
የግር አውራ ጣት እና የተቀጣዩ ጣት መሀል ሰፋ ያለ ርቀት አለ
አካለ ስንኩል ልጅ ምልክት የያዘችን ትንሽ ሴት ልጅን ትከሻው ላይ ተሸክሞ.
በንደዚህ አይነት ጊዜ የልጆቹን ጥንካሬ አግኙ

የወደ ሁዋላ በሽታ በናት ወይንም በሌላ ሰው ምክንያት ምክንያት የመጣ ነገር አይደለም። አንድ እናት ስታረግዝ ከ35 አመት በላይ ከሆነች ልጅዋ የወደ ሁዋላ በሽታ መያዝ አደገኝነት ከፍ ይላል። እነዚህ ልጆች ልክ እንደ ሁሉ ሕፃናት እንክብካቤ ያስፈልጋቸዋል በተጨማሪ አንዳንድ እንቅስቃሴ እነዚህን ልጆች መማር እንዲችሉ ይረዳል። ስለዚህ በደንብ ለመረዳት የሚቀጥለውን ሊንክ ተጫኑ፦ የገጠር አካለ ስንኩል ልጆች ምእራፍ 32 (In English).

የወደ ሁዋላ በሽታ ያላቸውን ልጆች እንክብካቤ

በአብዛኛውን የሰውነት ችግር ከቤተሰብ እና ከረዳት እርዳታ ጋር ማሻል ይቻላል። ከመድኃኒትም የበለጠ እነዚህ ልጆች ፍቅር፣ሀላፊነት፣እንክብካቤ እና የጨዋታ ግዜ ልክ እንደ ሁሉ ሕፃናት ያስፈጋቸዋል። እያንዳንዱ ሕፃን ያለውን ችሎታ እና ጉብዝና እዩ።

የልጆችን ደህንነት በደንብ ለመጠበቅ እናትን የመንከባከብን ያህል ጠቃሚ ነገር የለም

ተጨማሪ ሀይለኛ የወሊድ ችግሮች

አንዳንድ የወሊድ ችግሮች በጣም ኀይለኛ ከመሆናቸው የተነሳ አራስ ሕፃንን ይገላሉ። የሕፃን ሞት ቤተሰብን እና ዘመድን ሀዘን ውስጥ ይከታል። ስለዚህ የጤና ጠባቂ ሰራተኛ ቤተሰብ እና ዘመድን በማጽናናት መርዳት ይችላል።

NWTND Newb Page 10-1.png

ሕፃንን ማጽዳት እና ማልበስ

NWTND Newb Page 11-1.png
ብዙ እናቶች ልጆቻቸውን ከመጥፎ አየር ለመጠበቅ ብዙ ልብስ ወይንም ጦሊት በመደራረብ ይጠቀማሉ ግን ይህን ማረግ ሕፃንን በጣም ሊያሞቅ ይችላል። አንድ ጦሊት ወይንም ልብስ በቂ ነው።

የተወለደ ሕፃን ላይ ያለውን ደም እና የንግጄ ውሀ ጠራርጉ ግን አከላትን እንዳታጥቡ። ከሁለት ወይንም ሶስት ቀን በሁዋላ ልጅ ያገረሹትን ወተት እና አይነ ምድር ለማጽዳት የሕፃንን አከላት በየጊዜው ቤተሰብ ማጠብ አለበት።

ልጆችን ስታለብሱ ልክ እንደ ማንኛውም ሰው አልብሱና አንድ ተጨማሪ ልብስ ደርቡላቸው።ለመጀመሪያ አንድ/ሁለት ሳምንት የልጆቹን ጭንቅላት በደንብ ሸፍኑ ምክንያቱም ለሰውነታቸው ብዙ ሙቀታቸውን የሚያገኙት በራሳቸው በኩል ነው። የሕፃን ጨርቅ ወይንም ዳይቸር/ኩሽ እንደቆሸሸ ቶሎ በተቻለ ቀይሩ። የሕፃን ቆዳ ከቀላ ወይንም ከተንደበደበ ጨርቁን ወይንም ዳይፐሩን ለተወሰነ ጊዜ አታርጉላቸው።