Hesperian Health Guides
ትረሽ (thrush) ካንዲዳ(candida) እና ይስት ኢንፌክሽን (yeast infection)
የጤና ዊኪ > አዲሱ ሐኪም በሌለበት > ምዕራፍ 27: አራስ፡እና፡ጡት፡ማጥባት > ትረሽ (thrush) ካንዲዳ(candida) እና ይስት ኢንፌክሽን (yeast infection)
ጀንቲን ቫዮሌት(gentian violet)፣ጂቪ(GV)፣ክሪስታል ቫዮሌት(crystal violet) እና ሜትመይልሮሳኒሊየም ክሎራይድ(methylrosanilinium chloride)
ጀኒንታን ቫዮሌት(gentian violet) ውድ ያልሆነ ሕክምና የይስት ኢንፌክሽንን ለማከም በአፍ ሊሰጥ፣ የምታጠባ እናት ጡት ላይ ሊደረግ፣ የቆዳ እጥፋት ላይ፣እምስ ላይ ወይንም ውጨኛ እምስ ላይ ሊደረግ የሚችል ነው። በተጨማሪ አንዳንድ የቆዳ ባክቴርያ ኢንፌክሽኖች ላይ ይሰራል።
ቆዳን ሊያንደበድብ እና ቁስል አፍ ላይ እና እምስ ላይ ሊያመጣ ይችላል። መንደብደብ ወይንም ቁስል ከታየ መጠቀም አቁሙ።
ጀኒንታን ቫዮሌት(gentian violet) ሁሉን ነገር ወደ ወይን ጠጅ ይቀይራል። ከቆዳ ላይ ከትንሽ ቀን በኋላ እየለቀቀ ይሄዳል ግን ልብስን ያበላሻል።
ናይስታቲን(Nystatin)
ናይስታቲን(nystatin) አብዛኛው የይስት ኢንፌክሽንን አፍ ውስጥ፣የጡት ጫፍ ላይ፣ ቆዳ ላይ ወይንም እምስ ውስጥ ለማዳን ይረዳል። ለአፍ ውስጥ ናይስታቲን(nystatin) ፈሳሽ መድኀኒት በውኃ የሚበጠበጥ ዱቄት ወይንም እንሚመጠጥ ከረሜላ () ሊሆን ይችላል። ለቆዳ እንደ ቅባት ዘይት ወይንም እንደ ዱቄት ሊሆን ይችላል። ለእምስ ውስጥ ይስት ኢንፌክሽን ናይስታቲን(nystatin) እምስ ውስጥ መከተት እንደሚችል ክኒን ወይንም ክሬም ሊሆን ይችላል።
ናይስተቲን(nystatin) የተደረገበት ቦታ ላይ ሰውነትን ሊያስቆጣ ይችላል። የሰውነት መቆጣት የተለመደ ስላልሆነ መንደብደብ ከታየ መድኀኒቱን መጠቀም አቁሙ። አንዳንዴ ናይስተቲን(nystatin) ተቅማጥ ያመጣል።
ይስት ኢንፌክሽን በተደጋጋሚ ሲታይ እና በናይስተቲን(nystatin) የማይድን ሲሆን የኤች አይቪ(HIV) መያዝ ምልክት ሊሆን ይችላል።
ትረሽ(thrush) አፍ ውስጥ ላለው ሕጻን