Hesperian Health Guides

በአንቲባዮቲክ(antibiotics) ዓይንን ማከም

አራስ፡እና፡ጡት፡ማጥባት: መድኀኒቶች

እናት ጎነሪያ የአባለዘር በሽታ ካላት ከኀይለኛ ኢንፌክሽን እና ከመታወር ሕፃንን ሲወለድ/ስትወለድ ለመጠበቅ የአንቲባዮቲክ(antibiotics) ቅባቶች እና ጠብታዎች ይረዳሉ። በተጨማሪ የአንቲባዮቲክ(antibiotics) ቅባቶች እና ጠብታዎች ሌሎች የአይን ባክቴሪያ ኢንፌክሽኖችን ለማዳን ይረዳሉ። የአይን ኢንፌክሽኑ ኀይለኛ ከሆነ አንቲባዮቲክ(antibiotics) በአፍ ወይንም በመርፌ ስጡ።

አጠቃቀምNBgrneyedropoint.png

በተወለዱ ህጻኔት ላይ በመጠቀም ጎነሪያን ለመከላከል ከነዚህ አንዱን ቅባት ወይንም ጠብታን በሁለቱም ዓይን ላይ አርጉ። ከወሊድ በኋላ ላለ ኢንፌክሽን እና ከመካከለኛ የአይን ኢንፌክሽን ሕፃኑን ለመጠበቅ

1% ቴትራሳይክሊን(tetracycline) ወይንም ከ0.5% እስከ 1% ኢራይትሮሚሲን(erythromycin) ቅባት ይረዳል። ከወሊድ በሁዋላ ባለው 2 ሰዓት ውስጥ አንድ ጊዜ በቀጭን መስመር ቅባቱን በሁለቱም ፃይን ውስጥ አርጉ።

ቀስ ብላችሁ የታችኛውን የዓይን ሽፋን ወደታች ስባችሁ ቀጭን መስመር የሚሆን ቅባት ከውስጠኛው ወደዳር በኩል ድረስ አርጉ። የብልቃጡ ጫፍ የልጅትዋን አይን እንዳይነካ ተጠንቀቁ።


ይህ እነብ ቅባት ከሌለ ኢንፌክሽን ለማቆም ከሚቀጥሉት አንዱን ጠብታዎች ተጠቀሙ፦

የፖቪዶን አዮዳይን(povidone-iodine) 2.5% ሶልውሽን 1 ጠብታ ወይንም የሲልቨር ናይትሬት(silver nitrate) 1%

ሶልውሽን 1 ጠብታ ብቻ እያንዳንዱ አይን ላይ በተወለዱ በ2 ሰዓት ውስጥ መስጠት።
ር እየተነነ ኀይለኛ ስለሚሆን የቆየ ካላችሁ አትጠቀሙት። እርግጠኛ ካልሆናችሁ የሕፃንን አይን ስለሚያቃጥል አለመጠቀም የተመረጠ ነው።


የታችኛውን የዓይን ሽፋን ወደታች ስባችሁ አንድ ጠብታ ዓይን ውስጥ ጭለቁ። እቃው ወይንም ብልቃጡ አይን እንዳይነካ ተጠንቀቁ።