Hesperian Health Guides

ኮሮናቫይረስ — ኮቪድ -19

ኮቪድ-19 ምንድን ነው?

ኮቪድ-19 ኮሮናቫይረስ በሚባል ረቂቅ ጀርም (ያለ አጉሊ መነፅር በአይን የማይታይ) ምክንያት የሚመጣ እና ከሰው ሰው የሚተላለፍ በሽታ ነው፡፡ ኮቪድ-19 እንደ ደረቅ ሳል፣ የትንፋሽ ማጠር ወይንም ለመተንፈስ መቸገር ፣ ትኩሳት፤ የድካም ሰሜት እንዲሁም የሰውነት ህመም የመሳሰሉ የጉንፋን አይነት ምልክቶች አሉት፡፡ ኮቪድ-19 በዋናነት የመተንፈሻ አካልን የሚያጠቃ በሽታ ነው ፡፡ ምንም እንኳን አብዛኛውን ጊዜ ይህ በሽታ አደገኛ ባይሆንም፡ በሽታው ሊባባስ እና እንደ ሳንባ ምች (ከባድ የሆነ የሳንባ ኢንፌክሽን) ላሉ ከፍተኛ በሽታዎች በማጋለጥ ለሞት ሊዳርግ ይችላል፡፡

የኮሮናቫይረስ በሽታ እንዴት ይተላለፋል?

Corona color Page 1-1.png

የኮሮና ቫይረስ ወደ ሰውነታችን ውስጥ የሚገባው በአፋችን፤ በአፍንጫችን እና በአይናችን በኩል ነው፡፡ ይህም የሚሆነው በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች በአቅራቢያችን ሆነው በሚተነፍሱበት፤ በሚያስሉበት እና በሚያስነጥስበት ወቅት እንዲሁም በቫይረሱ የተበከሉ ነገሮችን ነክተን እጃችንን ሳንታተብ አይናችንን አፍንጫችንን ወይንም አፋቸንን በምንነካበት ወቅት ነው፡፡ አብዛኛውን ጊዜ ሰዎች ለቫይረሱ በተጋለጡ በ5 ቀናት ውስጥ የሕመም ምልክት የሚጀምራቸው ቢሆንም፤ ቫይረሱ በሰዉነት ውስጥ ከ2-14 ቀናት ምንም አይነት የህመም ምልክት ሳያሳይ ሊቀመጥ ይችላል፡፡ ቫይረሱ አንዳነድ ሰዎችን በተለይ ደግሞ ህፃናትን ይዟቸው ምንም አይነት ምልክትም ሆነ ህመም ሳያስከትልባቸው ሊቀር ይችላል፡፡ በዚህም ምክንያት አንዳነድ ሰዎች ጭራሽ የኮሮና ቫይረስ እንደያዛቸው ሳይታወቃቸው ለሌላ ሰው ቫይረሱን ሊያስተላልፉ ይችላሉ፡፡ የኮሮና ቫይረስ በአንዳነድ ቁሶች ላይ ቢያንስ ለ 3 ቀናት ምናለባትም ከዛ በላይም ለመኖር ይችላል፡፡ በንክኪ በቀላሉ የመተላለፍም አቅም አለው፡፡

የኮሮናቨይረስ ማንን ሊይዝ ይችላል?

ማንኛውም ሰው በኮሮናቫይረስ ሊያዝ ይችላል፡፡ በኮሮናቫይረስ አንዴ ተይዘው ካገገሙ በኋላ ቫይረሱ በድጋሜ ሊይዝዎት ሰለመቻል ወይንም አለመቻሉ እስከአሁን ድረስ በጥናት የተረጋገጠ ነገር የለም፡፡ እድሜቸው ከ45 ዓመት በላይ የሆኑ ሰዎች በተለይም አዛውነቶች፤ ሌላ ቀደም ያለ የጤና እክል በተለይም የመተንፈሻ አካል በሽታ ያላቸው እንዲሁም በሽታ የመከላከል አቅማቸው ደካማ የሆኑ ሰዎች ለኮሮናቫይረስ ተጋላጭነታቸው ከፍተኛ ከመሆኑም ባሻገር ለከፋ ህመምም ሊዳረጉ ይችላሉ፡፡

እራስዎን ከዚህ በሽታ እነዴት መጠበቅ ይችላሉ?

በአሁኑ ወቅት ለኮሮናቫይረስ ክትባትም ሆነ በቨይረሱ የተያዘን ሰው ለማዳን የሚያስችል መድሃኒት አልተገኘም፡፡ ኮሮናቫይረስ በአንቲባዮቲክም ሆነ በቤት ዉስጥ በሚዘጋጁ መድሃኒቶች ልንገድለው አንችልም፡፡ ኮሮና ቫይረስን ልንከላከለው የምንችለው ከቫረሱ ጋር ምንም አይነት ንክኪ እንዳይኖረን በማረግ በቻ ሲሆን እጃችንን አዘውትረን በመታጠብ ቫይረሱን ልንገድለው እንችላለን፡፡

  • እጅዎን በውሃ እና በሰሙና አዘውትረው ይታጠቡ ወይንም አልኮልነት ባላው የእጅ ንፅህና መጠበቂያ /ሳኒታይዘር/ ያፅዱ፡፡
    • እጅዎን በውሃ እና በሳሙና ለ20 ሰከንድ በደነብ እሽት አድርገው ይታጠቡ፡፡ ጥፍረዎን፤ መዳፍዎን፤ ጣቶችዎን፤ የክንድዎን መጅመሪያ ጨምሮ የእጅዎን አንጓ በደንብ በሰሙናው አሽተው ይታጠቡ፡፡
    • ምንግዜም ውጪ ቆይተው ወደቤትዎ ሲመለሱ፤ መፀደጃ ቤት ከተጠቀሙ በኋላ፤ ምግብ ከመመገብዎ በፊት፤ ካስነጠሰዎት፣ ካሳለዎት እንዲሁም ከተናፈጡ በኋላ እጅዎትን መታጠብ አይዘንጉ፡፡
    • እጅዎን ሳይታጠቡ በጭራሽ ፊትዎን አይንኩ፡፡
  • በኮሮና ቫይረስ ተይዘው ሊሆኑ የሚችሉ ሰዎች ነክተዋቸው ሊሆኑ የሚችሉ ቁሶችን (ለምሳሌ የበር እጀታዎችን፤ የሱቅ እና የካፌ መደገፊያ ጠረጴዛ/ ወለሎችን ወዘተ…) አልኮል ወይንም በረኪና በመጠቀም ያፅዱአቸው፡፡
    • አልኮል፡ ውህደቱ 70% የሆነ አይሶፕሮፔል አልኮል የኮሮና ቫይረስን በፍጥነት የመግደል አቅም አለው፡፡ ይህንን አይነቱን አልኮል በተለያዩ የንግድ ቦታዎች የሚገኙ መደገፊያ ባንኮኒዎች እና የበር እጅታ የመሳሰሉ ቁሳቁሶችን ለማፅዳት ይጠቀሙበት፡፡ ለበለጠ የማፅዳት ውጤት የአልኮል ውህዱ ከ60%-70% የሆነ እነጂ 100% አልኮል አይጠቀሙ፡፡ ምክንያቱም አልኮል ማንኛዉንም ጀርም ለመግደል ከውሃ ጋር መቀላቀል ስላለበት ነው፡፡ ያለዎት 100% አልኮል ከሆነ ለሁለት ብርጭቆ 100% አልኮል አንድ ብርጭቆ ውሃ በመጨመር ያዋህዱት፡፡ መንኛውንም ቁስ መጀመሪያ በዉሃና በሳሙና ካፀዱ በኋላ በአልኮል ውህዱ በድጋሜ በማፅዳት በአየር አንዲደርቅ ያድርጉ፡፡
    • በረኪና፡ በረኪና አብዛኛውን ጊዜ የሚዘጋጀው በ5% ውህድነት ነው ፡፡ የህንንም ውህድ መጠቀም ያለብን በቀዝቃዛ ውሃ ውስጥ በማቅጠን ሲሆን፤ በሙቅ ውሃ የቀላቀሉት እንደሆነ አይሰራም፡፡ ለመሬት እንዲሁም ሌሎች ሰፊ ወለሎችን ለማፅዳት በ20 ሊትር ውሀ 2 ብረጭቆ (500ሚሊ ሊትር) በረኪና በማዋሃድ ይጠቀሙ፡፡ አነስተኛ ወለሎችን ወይንም ሌሎች ቁሳቁሶችን ለማፅዳት በ1 ሊትር ውሃ ውስጥ 3 የሾርባ ማንኪያ በረኪና በመጨመር ይጠቀሙ፡፡መንኛውንም ቁስ መጀመሪያ በዉሃና በሳሙና ካፀዱ በኋላ በውሀ ባዋሀዱት በረኪና በድጋሜ በማፅዳት በአየር አንዲደርቅ ያድርጉ፡፡
  • አዘውትረው በእጅዎ የሚነኳቸውን ቁሶች በእነዚህ አይነት ፀረ ጀርም ውህዶች ያፅዷቸው፡፡
  • የተለበሱ ልብሶችዎን የሚያጥቡት በእጅዎ ከሆነ ሳሙናው በደንብ አረፋ እስኪያወጣ እያገላበጡ ይሹት፤ ከዛም አለቅልቀው በደንብ እስኪደረቅ ፀሀይ ላይ ያስጡት፡፡ የተለበሱ ልብሶችን በልብስ ማጠቢያ ማሽን የሚያጥቡ ከሆነ ቢቻል በትኩስ ውሀ እና ሳሙና ይጠቡዋቸው፡፡ ልብሱን የማጠቢያ መሽኑ ዉስጥ ካስገቡት በኋላ መሽኑ ልብሱን ማጠብ ከመጀመሩ በፊት አንደ ግዜ እንዲያለቀልቅ /ፕሪ-ሪንስ እንጊደርግ/ ይዘዙት፡፡
  • አፍ እና አፍንጫዎን በጭንብል በመሸፈን እራስዎን ከበሽታው መጠበቅ፡ አንድ በኮሮና ቫይረስ ተይዟል ተብሎ የሚታመን ሰውን እየተንከባከቡ የሚገኙ ከሆነ ከቀዶ ጥገና ጭምብል/ ሰርጂካል ማስክ/ የተሻለ ኤን 95 የተባለው ጭንብል በሽታው ወደእርስዎ እንዳይተላለፍ ይከላከላል፡፡ የአፍ እና የአፍንጫ መከለያ ጭንብል አግባብ ያለው አጠቃቀም፡
    • እጅዎትን በሳሙና እና በውሀ በደነብ መታጠብ ወይንም አልኮልነት ባለው ውህድ በማሸት ማፅዳት፤ ከዛም አፍ እና አፍንጫዎትን በጭንብሉ መሸፈን፤ በፊትዎ እና በጭንብሉ መካካል ክፍተት አለመኖሩን ማረጋገጥ፡፡
    • ጭንብሉን ካደረጉት በኋላ በእጅዎ አይነካኩት፤ በትንፋሽዎ የረጠበ እንደሆነ ሌላ አዲስ ጭንበል ቀይረው ያድርጉ፡፡
    • ጭንብሉን ለማውለቅ ሲፈልጉ ከበስተጀርባ የሚያርፈውን የላስቲክ ገመድ በመያዝ ያውልቁ (ጭምብሉን ግን በጭራሽ በእጅዎ አይነኩት)፤ ጭንብሉን ካወለቁት በኋላ ወዲያዉኑ ወደቆሻሻ መጣያ በመጣል እጅዎን በደንብ ያፅዱ፡፡
    • አንድ ጊዜ የተጠቀሙበትን ጭንብል በድጋሜ አይጠቀሙ፡፡ በድጋሜ መጠቀም ግድ ከሆነብዎ ግን የህንን የኤን 95 ጭንብል ከማንኛውም ህዋስ ፅዱ ለመድረግ ለ 30 ደቂቃ ያህል 72° ሴነቲ ግሬድ በሚደረስ ሙቀት ያስመቱት፡፡ ቢያንስ 5 የኤን 95 ጭንብል ካለዎት ለአምስት ተከታታይ ቀናት እየቀያየሩ ለማድረግ አንድ ቀን የተጠቀሙትን ጭንበል ለብቻው በአንድ ቦርሳ እነዲታፈን አድርገው ለ5 ቀናት ካስቀመጡት በኋላ እንደገና ሊጠቀሙበት ይችላሉ፡፡
    • በኮሮናቫይረስ የታመሙ ሰዎችን በሚንከባከቡበት ጊዜ ከጨርቅ የተሰሩ ጭምበሎችን እንደ አማራጭ መጠቀም በፍፁም አይመከርም፡፡ ምክንያቱም ጨርቁ በትንፋሽዎ ሙቀት በሚረጥብበት ጊዜ ከታማሚው ትንፋሽ ጋር የሚወጡ እርጥበት አዘል ብናኞች በቀላሉ ወደ ውስጡ ሊያስገባና ለበሽታው ሊያገልጥዎ ስለሚቸል ነው፡፡
  • ሌሎች ሰዎች ለቫይረሱ ተጋላጭ እንዳይሆኑ እርስዎ አፍ እና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብልዎን ያድርጉ፡ ሰዎች በኮሮናቫይረስ መያዛቸውን ሳያውቁ ነገር ግን ተይዘው ሊሆን ስለሚችል ሁሉም ሰው ከቤቱ ሲወጣ ቀለል ያለ ከጨርቅ የተሰራ የአፍ እና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል ቢያደርግ ቫይረሱ ከአንዱ ሰው ወደ ሌላ ሰው እነዳይተላለፍ ያደርጋል፡፡ ክትባት እስካለተገኘለት ድረስ ማህበረሰባችንን ከኮሮናቫይረስ ልንታደገው ምንችለው ቨይረሱን ከመሰራጨት በመከላከል ብቻ ነው፡፡ በተጨማሪም እጅዎን አዘውትረው በመታጠብ እና ከሰዎች ምንግዜም 2 ሜትር (6 ጫማ) ይራቁ ፤ ምክንቱም እርስዎ የሚያደረጉት ጭምበል ባቅራቢዎ የሚገኙ ሰዎች አንጂ እርስዎን ለቫይረሱ ከመጋለጥ አይጠብቅዎትም፡፡
  • የጤና ሁኔታዎትን ያስተውሉ፡፡ ደረቅ ሳል፤ ለመትንፈስ መቸገር፤ የደረት ህመም ወይንም የመጫን ስሜት እና ትኩሳት የመሳሰሉ ምልክቶችን ካስተዋሉ በአስቸኳይ የኢትዪጵያ ጤና ጥበቃ ሚኒስተር ባዘጋጀው ነፃ የስልክ መስመር (8335) ለይ በመደወል አስፈላጊውን ክትትል የት ማግኘት እንደሚችሉ እና ምን አይነት ቅደም ተከተሎችን መከተል እንደለብዎት መመሪያ ያግኙ፡፡ ይህንንም ማድረግ ያለብን የኮቪደ-19 ከፍተኛ የህመም ደረጃ ሙሉ በሙሉ መተንፈስ ስለሚከለክል እና ይህንንም ለማከም የሚቻለው ለዚሁ በሽታ እንክብካቤ ለማድረግ ዝግጁ በሆኑ የማስተንፈሻ ማሽኖች/ቬንትሌተር/ እና ኦክስጂን ባላቸው የጤና አገልገሎት መስጫዎች ብቻ ስለሆነ ነው፡፡
    • ይሕ ገፅ መጨረሻ የተሻሻለበት ቀን፡05 ጃንዩ. 2024