Hesperian Health Guides

ጡት ማጥባት

ይህ ምእራፍ ውስጥ፦

NWTND Newb Page 18-1.png

የመጀመርያ ጊዜ የወለደች እናት ጡት ማጥባት ላይ እርዳታ ያስፈልጋት ይሆናል። ረጋ እንድትል እና፣ እንድታስተውል አርጓት። ወደላይ በትራስ ወይም በሳንባ ምች ልብስ ከፍ እንድትል አርጋችሁ አበረታትዋት። ቤተሰብ እና ጐረቤት እናት ለማጥባት ጊዜ እንዲሰጥዋት ጠይቁ። ጡት ማጥባት ከልማድ እና ከጊዜ ጋር ቀላል ይሆናል።

ለሕፃን ከጡት ወተት ሌላ የበለጠ/የተሻለ አይነት የተበጠበጠ ወይንም ፎርሙላ ወተት የለም።

የጡት ጫፍ አከፋፈት የሚያም እንዳይሆን የጡት ማጥባት አደራረግና አፍ ውስጥ አከታተትን ማወቅ ይረዳል። የሕፃንን ሰውነት ባጠቃላይ ወደ እናት አዙሩ የሕፃንዋ አንገት እንዳይጣመም። ሕፃንዋ አፏን በደንብ ስትከፍት ወደ ጡት አስጠጓት። የጡት ጫፍ እና ዙርያውን ያለው ጠቆር ያለው ቦታ ሕፃንዋ አፍ ውስጥ በደንብ መግባት አለበት።

NWTND Newb Page 18-3.png
የጡቱ ጫፍ የሕፃን ዓፍ ውስጥ በደንብ ገብቶ
የታችኛው ለንቦጭ ወደ ታች ታጥፎ
አፉን/አፏን በደንብ እስኪከፈት
ወደ እናት ሰውነት ሕፃን ቅርብ ተይዛ
NWTND Newb Page 18-2.png
እንደዚህ እንደዚህ አይደለም። ይህ አይነት አጠባብ የሚያም የጡት ጫፍ አከፋት ሊያመጣ ይችላል

የመጀመርያው የእናት ጡት ወተት እንደ ፈሳሽ ወርቅ ነው

የመጀመርያው የእናት ጡት ወተት ኮለስትረም ይባላል። ይህ ወተት ትንሽ በትንሽ ነው የሚመጣው ግን ለአዲስ ለተወለደ ሕፃን በቂ ነው (የሕፃን ሆድ የተወሰኑ ሻይ ማንኪያዎች ነው በአንዴ መያዝ የሚችለው)። የመጀመርያው የእናት ጡት ወተት የሚያጣብቅ እና ቀለሙ ቢጫማ ነው ነገር ግን ከዛ የበለጠ በጣም ጠቃሚ ምግብ ለአዲስ ሕፃን የለም። ይህ የእናት ጡት ወተት እናት ሰውነት ውስጥ የተሰራ (አንቲ ቦዲ) ሲሆን ሕፃንን ከኢንፌክሽን የሚጠብቅ ነገር አለው። ጥሩ አይደለም ብላችሁ ይህንን ወተት እንዳትጥሉ ምክንያቱም ይህ ከየትኛውም መድኃኒት የበለጠ ለሕፃን ጠቃሚ ነው።የመጀመርያው 2 ቀን ጡት ማጥባት ያስፈልጋል ምክንያቱም ጠቃሚውን ወተት ከሳስት ቀን በሁዋላ የእናት ሰውነት መስራት እንዲጀምር። ሕፃን በደንብ ሲጠባ የእናት ሰውነት ተጨማሪ ወተት ይሰራል።

ልጁ በቂ ወተት እያገኘ ነው?

ማንም ሰው በቂ ወተት ለሕፃንሽ የለሽም ብሎ አያሳምናችሁ። በተለይ ሰውነት ወተት መስራት በሚጀምርበት ቀናት ውስጥ።

አንዳንድ ግዜ በራስ ባለመተማመን እና በሰዎች ግፊት እናት፣አያት፣አክስት ወይንም ረዳትዋ ነርስ ፎርሙላ፣አጃ ወይንም ሌላ ምግብ ለአዲስ ሕፃን (ከተወለደ ብዙ ላልቆየ) ይሰጣሉ። እነዚህን ምግባች መግዛት እና መስራት ጥቅም የለውም በተጨማሪ ለሕፃን ተቅማጥ ሊያመጣ ይችላል። ተቅማጥ ሕፃንን ኪሎ እንዲቀንስ እና ደካማ እንዲሆን ያረጋል። ይህንን ምግባች መጠቀም እናት ሕፃንዋን በጡት ወተት በቂ መመገብ እማትችል እንዲመስላት እና የእናት ሰውነት አነስተኛ ወተት እንዲሰራ ያረጋል። የጤና ጥበቃ ሰራተኞች ከሆናችሁ እናቶች ሕፃንን በማጥባት መመገብ እንደሚችሉ በማሳመን ይህንን አይነት የጤና ችግርን ማስወገድ ልትረዱ ትችላላችሁ። እናትን ሕፃንን ለማጥባት ማስተካከል እርድዋት ግን እናት ለብቻዋ ማጥባት እንድትችል፣ ረጋ እና ቀስ ብላችሁ አስረድዋት በተጨማሪም ጊዜ ስጥዋት ።

በቂ ወተት ለመስራት

  • ቶሎ ቶሎ አጥቡ -ብዙ ባጠባችሁ ቁጥር ብዙ ወተት ሰውነት መስራት ይቻላል።
  • በቂ ፈሳሽ ጠጡ እና በቂ ተመገብ-እራስን መመገብ ሕፃኑን እንደመመገብ ነው።
  • እረፉ -አባትና ቤተሰብ ከረዱ እናት በቂ ረፍት ስለምታገኝ በደንብ ሕፃኑን መንከባከብ ትችላለች።

ብዙ ባጠባችሁ ቁጥር ብዙ ወተት ይኖራል

የመጀመርያው ሳምንት የአብዛኛውን ሕፃን ኪሎ ትንሽ ይቀንሳል። ከዛ በኋላ ግን ሕፃን ኪሎ ሲቀንስ በቂ ምግብ አላገኘም ማለት ነው። የመጀመርያ ቀናቸው ላይ ሕፃኖች ብዙ ሽንት አይሸኑም ግን ከዛ በኋላ በየተወሰነ ሰዓት ውስጥ መሽናት ይጀምራሉ። በየተወሰነ ሰዓት ካልሸኑ ከ2 ቀን በኋላ በቂ ወተት አላገኙም ማለት ነው። በደንብ ሕፃን እየጠባ በየተወሰነ ሰዓት ውስጥ ካልሸና የእናት ወተት በሌላ አይነት ወተት መተካት ሊያስፈልግ ይችላል። ስኳር በውሀ ወይንም የሩዝ ውሀ እንዳትሰጡ። አስፈላጊውን ያህል የሚበጠበጥ ወተት መግዛት ካልተቻለ ለሕፃን መስጠት አትጀምሩ (ለማብቃቃት ተብሎ ውሀ ማብዛት ተቅማጥ እና ህመም ያመጣል)። በተጨማሪ ጠርሙሳችን ለማጽዳት ከባድ ስለሆኑ እና የተቅማጥ ጀርም ሊያስፋፋ ስለሚችል ጠርሙስ አትጠቀሙ።

እናት አርፋ ከሆነ፣ከሕፃን ተለይታ ሌላ ቦታ ከሆነች ወይንም አንዳንዴ የእናት ሰውነት በቂ ወተት መስራት ካልቻለ ሌላ አይነት ወተት መሰጠት ሊያስፈልግ ይችል። ሌላ እናት ጡት እንድታጠባ መጠየቅ ይቻላል ግን የምታጠባው እናት ኤችአይቪ እንደሌላት ማረጋገጥ ያስፈልጋል። አማራጭ ከሌለ ደግሞ የከብት ወተትን ቀጥሎ እንደሚገለጸው አርጎ መስጠት ይቻላል፦

አቀላቀል፦

ከላይ 2ቱ ግማሽ የላም ወይንም የፍየል ወተት
NWTND Newb Page 20-1.png
1 ውሀ
1 ትልቅ ማንክያ ስኳር

ወይንም
1 የበግ ወተት
1 ውሀ
1 ትልቅ ማንክያ ስኳር

ወይንም
2 የጣሳ ወተት (ስኳራማ/እንዲጣፍጥ ያልተደረገ)
3 ውሀ
እና 1 ትልቅ ማንክያ ስኳር

ጀርም ለመግደል የተበጠበጠውን ፎርሙላ ለተወሰነ ጊዜ አፍሉት ይህንን በማድረግ ጀርምን ማስወገድ ይቻላል። ከቀዘቀዘ በኋላ ለሕፃን በንጹህ ጠርሙስ ወይንም ማንኪያ መግቡ።

የጡትን ወተት በጅ ማውጣት (ወተት ማውጣት)

NWTND Newb Page 20-2.png

በስራ ምክንያት ወይንም በሌላ ምክንያት እናት ከሕፃን መለየት ካለባት ወተት አውጥታ ከሄደች ባትኖርም ሌላ ሰው ወተቱን ለሕፃን መስጠት ይችላል።

  1. እጅን እና ጠርሙሱን በደንብ እጠቡ ከተቻለ ወተት የሚደረግበትን ጠርሙሱን በውሀ ቀቅሉ
  2. የጡት ወተት ጠርሙስ ውስጥ ሲከተት
  3. የጡቱ ጠቆር ያለውን ዙርያ በአውራ ጣታችሁን እና በሌሎች ጣታችሁን ያዙና ወደ ደረታችሁ ገፋ አርጉ። ወተት ስታወጡ ረጋ ብሎ ስለ ሕፃን ማሰብ ይረዳል።

    በጣም ሙቅ ቦታ ካልሆነ የጡት ወተት ወደ 8 ሰዓት መቆየት ይችላል። የጡት ወተት ቀዝቃዛ ቦታ ከተደረገ ከስምንት ሰዓት በላይ ሊቆይ ይችላል።

ትረሽ (thrush)

NWTND Newb Page 21-1.png
ትንሽ ንጹህ ጨርቅ ሕፃኑ አፍ ውስጥ መድሐኒቱን ለመቀባት ተጠቀሙ

ነጭ እብጠት ወይንም ሽፍታ ምላስ ላይ ወይንም የውስጠኛው ጉንጭ ላይ ትረሽ (thrush) የተባለ የይስት ኢንፌክሽን ምልክት ነው። ይህ ኢንፌክሽን ከሕፃን አፍ ወደ እናት ጡት ጫፍ ተላልፎ ሊያሳክክ፣ሊያሳምም እና ሊያቀላ/ሊያቆስል ይችላል።

የጡት ጫፍን በቆምጣጤ አጠብ/ለቅለቅ አርጋችሁ ከዛ በድጋሚ በውሀ ለቅልቁት። ቆምጣጤ ከሌለ ባጠባችሁ ቁጥር ቀስ ብላችሁ በውሀ የጡት ጫፍን ለቅልቁ/እጠቡ እና አድርቁት። ይህ እንክብካቤ ትረሹን ካላዳነ የጡት ጫፍን ጀንቲያን ቪዮሌት( gentian violet) የተባለውን መድኃኒት በቀን 2 ጊዜ ቀቡት ለ3 ቀን። በተጨማሪ የሕፃንን የውስጥ አፍ በቀን አንዴ ቀቡት። (ይህ መድኃኒት ሁሉን ነገር ወይን ጠጅ ያረጋል ግን ምንም ችግር/ጉዳት አያመጣም።) ጀንቲያን ቪዮሌት ካልረዳ ለሕፃን ናይስታቲን(nystatin) ስጡ።

ትረሹ በተደጋጋሚ ከመጣ የሕፃንን ሰውነት እያደከመው ያለ ሌላ ነገር ሊሆን ይችላል በተደጋጋሚ ትረሹ እንዲመጣ ያደረገው። ለምሳሌ ልጆች ኤችአይቪ ካላቸው ትረሽ (thrush) በተደጋጋሚ ሊታይ ይችላል። ለተጨማሪ ማብራሪያ ኤችአይቪ እና ኤድስን እዩ (በመቀናበር ላይ ነው)

የጡት ህመም፣እብጠት፣መዘጋት፣ወይንም ኢንፌክሽን

NWTND Newb Page 21-2.png

አንዳንዴ የጡት ወተት የሚወጣበትን የሰውነት ውስጥ ቱቦ ይዘጋል። ይህ ሲከሰት ጡት ያብጣል፣ይቀላል/ይጠቁራል፣ እና ያማል ከዛ በመቀጠል ኢንፌክሽን ሊጀምርም ይችላል።

ምልክቶች
  • የሚሞቅ እና የጠቆረ/የቀላ ጠንካራ ነገር ጡት ላይ
  • ጡት ውስጥ ወይንም በማጥባት ላይ ሲያም

ትኩሳት ካለ የተዘጋው ወተት የሚያልፍበት ቱቦ ኢንፌክትድ ሆንዋል ማለት ነው።

ህክምና
  • እረፍት እና ብዙ ፈሳሽ መጠጣት
  • በየ2 ሰዓት ጡት ማጥባት፦ ኢንፌክትድ በሆነ ጡት ማጥባት ለሕፃን ጉዳት የለውም በተጨማሪ ኢንፌክሽኑ እንዲወጣ በጣም ጠቃሚ ነገር ነው።
እናት ጡት እያጠባች ጡትዋን ወደታች ማሳጅ/አሸት ስታረግ
ጠንከር ያለ አስተሻሸት/ማሳጅ አርጉ የተዘጋውን ቦታ ለመክፋት
  • ለማጥባት ጥሩ ወይንም የሚያመች ቦታ ካገኛችሁ በኋላ የሕፃንዋን ሰውነት ወደ እናት እንዲዞር አርጉ። የሕፃንዋ አፍ በደንብ ከተከፈተ በኋላ የእናት ጡት ጫፍ በደንብ የሕፃንዋ አፍ ውስጥ መግባት አለበት
  • በሚያመው/በዛለው በኩል መጀመርያ አጥቡ ሕፃንዋ የዛን ጡት ወተት እንድትጨርስ
  • የሞቀ ጨርቅ ወይንም ሞቅ ባለ ገንዳ ውስጥ መታጠብ ይረዳል ጡትን በቀን 4 ጊዜ ከ15 እስከ 20 ደቂቃ ያህል አሙቁ ወይንም ቀዝቀዝ ያለ ጨርቅ ወይንም የሰላጣ ቅጠሎች ጡት ላይ እብጠቱ እንዲቀንስ አርጉ።

እራስ ምታት (ትኩሳት) ካለ 250ሚሊ ግራም ኢራይትሮሚሲን(erythromycin) በቀን 4 ጊዜ ስጡ።

ኤች አይቪ(HIV) እና ጡት ማጥባት

ኤች አይቪ(HIV) ያላት እናት እንድትጠነክር እና ቫይረሱ ወደ ሕፃን እንዳይተላለፍ የሚያረግ መድኃኒት መውሰድ ትችላለች። ልጆችን እና እናቶችን ለመጠበቅ ሁሉ እርጉዝ ሴቶች ኤች አይቪ(HIV) ቴስት ቢያረጉ ጠቃሚ ነው። እርጉዝ ሴት ኤች አይቪ(HIV) ካላት አስፈላጊ መድኋኒቶችን መውሰድ በርግዝናዋ ግዜ እና ጡት በምታጠባበት ጊዜ ጠንካራ/ብርቱ ለመሆን እና በሽታው ወደ ልጅ እንዳይተላለፍ ይረዳል። ከዛም በኋላ መድሓኒቱን መውሰድ የናትን ጤንነት(ብርታት እና ጥንካሬን) ለመጠበቅ ይረዳል። ለተጨማሪ ማብራሪያኤች አይቪ(HIV) እና ኤድስን እዩ (በመቀናበር ላይ ነው)

እናት ኤች አይቪ(HIV) እያላት ጡት ማጥባት አደገኛ አይደለም?

የኤች አይቪ(HIV) መድሐኒት እናት እና ልጅ ሲወስዱ እናት ጡት በምታጠባበት ጊዜ ኤች አይቪ(HIV) ወደ ሕፃኑ እንዳይተላለፍ ይረዳል። ሕፃኑ በየቀኑ የኤች አይቪ(HIV) መድሐኒቶች ለ6 ሳምንት መውሰድ አለባቸው። እናት የኤች አይቪ(HIV) መድሓኒት በርግዝና ጊዜ ከመጀመርያ ጀምሮ ካልወሰደች ለህፃኑ 12ሳምንት የኤች አይቪ(HIV) መድሓኒት ስጡ። ጡት ማጥባት ለ6 ወር (ወይንም የሕፃኑ የመጀመርያ ጥርስ እስኪወጣ ድረስ) የሕፃንን ጤና ይጠብቃል። ከ6 ወር በፊት አጥሚት ወይንም ሌላ የሚበጠበጥ መጠጥ ለሕፃን ጤና እንደ እናት ጡት ወተት ያህል ጥሩ አይደለም በተጨማሪም የኤች አይቪ(HIV) ኢንፌክሽን መከሰትን ሊጨምር ይችላል።

የኤች አይቪ(HIV) መድኃኒት የእናት እና የሕፃንን ጤና ለመጠበቅ ጠቃሚ ነው

የኤች አይቪ(HIV) መድኃኒት ከሌለ ኤች አይቪ(HIV) ከእናት ወደ ሕፃኑ ሊጋባ ይችላል። ግን የተበጠበጠ ወተት መስጠትም ለሕፃኑ ጤና መታወክ አደገኛነት ሊኖረው ይችላል። ምክንያቱም እናት ንጹህ ውሀ፣ጋዝ እና በቂ ገንዘብ ፎርሙላ ለመግዛት ወይንም ለማዘጋጀት ከሌላት ልጆች ፕሮቲን በማጣት ወይንም በተቅማጥ ሊሞቱ ይችላሉ። በጥንቃቄ ፎርሙላ መሰጠት ካልተቻለ የእናት ጡት ወተት መስጠት ኤች አይቪ(HIV)ም መድኃኒት ባይኖርም የተመረጠ ነው።

ሁሉ ቦታ ለልጆች እና ለናት ጡት ማጥባት የተመረጠ ነው

ጡት ማጥባት

NWTND Newb Page 23-1.png
  • ወጪ የለውም እንደ ፎርሙላው ጠርሙስ እና ሌሎች ነገሮችን መግዛት አያስፈልግም
  • የእናት የወሊድ ደም መፍሰስን ለማቆም ይረዳል
  • ከወሊድ በኋላ ያሉት ወራት ውስጥ እርግዝና እንዳይከሰት ይረዳል
  • ከካንሰር እና ከአጥንት ጥንካሬ ድክመት ወደፊት እናትን ይጠብቃል
  • ሁሌ ጥሩ ነው፣ ሙቅ ነው፣ እና ሁሌም ለሕፃን ዝግጁ ነው
  • ለሕፃን ጤና አስፈላጊ የሆኑ ቫይታሚን እና ኒውትሪሽን አለው
  • ከተቅማጥ፣ ከንሞንያ እና ከሌሎች በሽታዎች ሕፃንን ለመጠበቅ ይረዳል
  • ሕፃንን ከስኳር በሽታ፣ ከአለርጂ እና ከካንሰር ወደፊት ይጠብቃል
  • ሕፃንን ከናት ጎን ደህና እና ሙቅ አርጎ ይጠብቃል
  • እናት እና ሕፃንን ቅርብ ያረጋል
NWTND Newb Page 23-2.png