Hesperian Health Guides

ደም መፍሰስን በአራሳች ላይ ማቆም

አራስ፡እና፡ጡት፡ማጥባት: መድኀኒቶች

ቫይታሚን “ኬ" (vitamin K)፣ ፓይቶመናዲዮን (phytomenadione) ፣ፓይቶናዲዮን (phytonadione)


ሰውነት ቫይታሚን “ኬ”ን (vitamin K) በመጠቀም ደምን በማርጋት ደም መፍሰስን ያቆማል። አራሶች ሲወሰዱ ሰውነታቸው ውስጥ ብዙ ቫይታሚን “ኬ"(vitamin K) የለም ስለዚህ በአንድ ምክንያት ደም መፍሰስ ከጀመራቸው ከቁጥጥር ውጪ ሊሆን ይችላል። አራስ ከየትኛውም የሰውነት ክፍል (ከአፍ፣ከእትብት፣ከመቀመጫ ቀዳዳ) ደም መፍሰስ ከጀመረው ቫይታሚን “ኬ"ን(vitamin K) በመስጠት ደም መፍሰስን በቁጥጥር ማድረግ ይቻላል። በተጨማሪ ለትንሽ ወይንም ከጊዜያቸው በፊት ለተወለዱ (ከ2 ኪሎ ግራም በታች) ሕፃኖች ብዙ ጊዜ ሊደሙ ስለሚችሉ ቫይታሚን “ኬ"(vitamin K) በመስጠት ከደም መፍሰስ መጠበቅ ይቻላል። ቫይታሚን “ኬ"(vitamin K) ከፍ ባሉ ልጆች ወይንም በትልቅ ሰው የሚከሰት የደም መፍሰስ አያቆምም።

አጠቃቀምNBgrninject.png

1ሚሊ ግራም (1ሚሊ ግራም አምፑል ወይንም 1/2 ከ2ሚሊ ግራም አምፑል) ቫይታሚን “ኬ"(vitamin K) አራስ በተወለደ በ2 ሰዓት ውስጥ የውጭኛው ታፋ ላይ በመርፌ ስጡ።

ተጨማሪ እንዳትከትቡ ጥቅም የለውም ተጨማሪ መስጠት ትርፉ ጉዳት ሊያስከትል ይችላል።